Sekela woreda Road and Transport Office Cell

Sekela woreda Road and Transport Office Cell Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Sekela woreda Road and Transport Office Cell, Sekela, Sekela Gish Abay.

06/04/2023
06/04/2023
06/04/2023

"አልማ ከዕቅድ ጀምሮ እስከ ፕሮጀክት ትግበራ ድረሰ ማህበረሰብ አሳታፊነቱ የማህበሩን ከፍታ በተግባር ያሳየ ነው" (አቶ አለባቸው ገነት= የምዕራብ ጎጃም ዞን ብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊና የአልማ ኮሚቴ አስተባባሪ)
~~~~~~
የምዕራብ ጎጃም ዞን አልማ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት የማህበረሰብ አቀፍ ፕሮጀክቶችን በውጤታማነት ለመፈፀም የሚያስችል ውይይት ከባለድርሻ አካላት ጋር አድርጓል።

በውይይቱ ተገኝተው መድረኩን የመሩት የምዕራብ ጎጃም ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊና የአልማ ኮሚቴ አስተባባሪ አቶ አለባቸው ገነት እንደተናገሩት የአልማን ህዝባዊነት የበለጠ ማስፋት፣ የፕሮጀክት አፈፃፀምን ማሳደግና ልምዶችን መቀመር እንደሚገባ ተናግረዋል።

አቶ አለባቸው ገነት አክለውም አልማ ከዕቅድ ጀምሮ እስከ ፕሮጀክት ትግበራ ድረሰ ማህበረሰብ አሳታፊነቱ የማህበሩን ከፍታ በተግባር ያሳየ፤ የክልላችንን የማህበራዊ ልማት ክፍተቶችን የሚሞላ ህዝባዊ መሠረት ያለው የልማት ማህበር ነው ብለዋል።

West Gojjamzone prosperity

03/04/2023

"የኢትዮጵያን ህዝቦች አንድነት ሊንድ የሚችል የሚዲያ አጠቃቀምን መግራት ያስፈልጋል"
********
የምዕራብ ጎጃም ዞን ብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ከዞን የመምሪያ የመንግስት ሰራተኛ የብልፅግና ፓርቲ አባላት ጋር "ድሎችን የማፅናትና ፈተናዎችን የመሻር ወቅታዊ ኦና ታሪካዊ አመራር ተልዕኮ" በሚል መሪ ቃል አካሂዷል።

በመድረኩ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የምዕራብ ጎጃም ዞን ብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አባይ አለሙ እንደተናገሩት የኢትዮጵያን ህዝቦች አንድነት ሊንድ የሚችል የሚዲያ አጠቃቀምን መግራት ያስፈልጋል፤ ለዚህ ዋነኛ ምከንያቱ ደግሞ የሚዲያ ነፃነትን በውል ካለመረዳት የሚመነጭ ነው ብለዋል።

በመሆኑም በሃገራችን የሃሳብ ልዕልና ወይም በዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ላይ የሚያተኩር፣ ህዝብን ከህዝበ የሚያቀራርብ እና የጋራ መግባባትን የሚፈጥር፣ የህዝብን ሠላምና ደህንነት ስጋት ላይ የማይጥል፣ ወንድማማችነትና እህትማማችነት ላይ የሚያተኩር ስራ የሚዲያ ስራን መከተል ይገባል።

አቶ አባይ አለሙ አክለው እንደገለፁት ሃገራዊ የውስጥ አንድነትን የሚሸረሽርና በህዝባችን ዘንድ ለዘመናት የተጋመደውን አንድነት ሊንድ የሚችል የሚዲያ አጠቃቀምን መግራት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።

West Gojjamzone prosperity

"የትራንስፖርት ዘርፍ መዘመንና በህግ አግባብ መመራት ለአንድ አገር ኢኮኖሚ መለወጥ ድርሻው የላቀ ነው" (አቶ ጌታየ ፈንቴ = የምዕራብ ጎጃም ዞን ትራንስፖርት ተ/ጽ/ቤት ኃላፊ)   *****...
03/04/2023

"የትራንስፖርት ዘርፍ መዘመንና በህግ አግባብ መመራት ለአንድ አገር ኢኮኖሚ መለወጥ ድርሻው የላቀ ነው" (አቶ ጌታየ ፈንቴ = የምዕራብ ጎጃም ዞን ትራንስፖርት ተ/ጽ/ቤት ኃላፊ)
******
የምዕራብ ጎጃም ዞን ትራንስፖርት ተጠሪ ጽህፈት ቤት የ2015 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወር ዕቅድ አፈፃፀም በፍኖተሰላም ከተማ በዛሬው ዕለት ገምግሟል።

የዞን የዘርፍ አመራሮችና ባለሙያወች፣ የወረዳዎች እና የከተማ አሰተዳድሮች የማኔጅመንት አባላት ተሳታፊ በሆኑበት በዚህ መድረክ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የምዕራብ ጎጃም ዞን ትራንስፖርት ተጠሪ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጌታየ ፈንቴ እንደተናገሩት የትራስፖርት ዘርፉ መዘመን እና በህግ አግባብ መመራት ለአንድ አገር ኢኮኖሚ መለወጥ ድርሻው የላቀ እንዳለው ተናግረዋል።

አቶ ጌታየ ፈንቴ አክለው በቀጣይ በትራንስፖርት ዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን መፍታት የሚያስችል ስራ መስራት እንደሚያስፈልግ ገልፀው የመንገድ ትራፊክ ደህንነትን በተመለከተ የህብረተሰቡንና የአሽከርካሪዎችን ግንዛቤ ከማሳደግ ባሻገር የትራፊክ ቁጥጥር ስራ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ የሚሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።

West Gojjamzone prosperity

"አቅማችንን በማስተባበር የህዝቡን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ አለብን" (አቶ መልካሙ ተሾመ= የምዕራብ ጎጃም ዞን ዋና አስተዳዳሪ)  *********የምዕራብ ጎጃም ዞን ግብርና መምሪያ ከ...
26/03/2023

"አቅማችንን በማስተባበር የህዝቡን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ አለብን" (አቶ መልካሙ ተሾመ= የምዕራብ ጎጃም ዞን ዋና አስተዳዳሪ)
*********
የምዕራብ ጎጃም ዞን ግብርና መምሪያ ከወምበርማ ወረዳ ግብርና ጽህፈት ቤት ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የበጋ መስኖ የመስክ በዓል አዘጋጅቶ በወምበርማ ወረዳ ዋዝ ዝንግስ ቀበሌ ተካሂዷል።

በመስክ ጉብኝቱ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የምዕራብ ጎጃም ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መልካሙ ተሾመ እንደገለፁት በዞናችን ያሉትን ፀጋዎች በመጠቀምና አቅማችንን በማስተባበር የህዝቡን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ አለብን ብለዋል። ለዚህ አንዱና መሠረታዊው ተግባር የበጋ መስኖ ሰንዴ ልማት መሆኑንም አቶ መልካሙ ተናግረዋል።

የዘንድሮው የበጋ መስኖ ስንዴ አፈፃፀማችን የላቀ ውጤት ያገኘንበት ቢሆንም እንደዞን ካሉን ፀጋዎች አኳያ ጀመርነው እንጂ ወደፊት ከዚህ በበለጠ መስራት እንደሚገባ ገልፀው በዚህ ዓመት በሁሉም ወረዳዎች የተጀመረው የበጋ መስኖ ስንዴ ስራ በመኸር ወቅት በምናገኘው ምርት ላይ ተደማሪ የኢኮኖሚ አቅም የምንፈጥርበት መሆኑንም ተናግረዋል።

west gojjam prosperity

26/03/2023

ብልጽግናም በፈታኝ ሁኔታ ውስጥ ባለችው አገራችን ከየትኛውም ጽንፍ ሳይወግን ችግሮችን ተቋቁሞና መስዋዕት ከፍሎ ኢትዮጵያን ለማሻገር ቆርጦ የተነሳ ፓርቲ ነው፡፡

በኢትዮጵያ የነበረውን ኢፍትሃዊ ተሳታፊነትና አካታችነት የጎደለው አካሄድ በመለወጥ ሁሉም እኩል የሚሳተፍበትና የሚወከልበትን እድል በመፍጠር በኢህአዴግ ውስጥ የነበሩ ችግሮችን በተግባር መፍታት የቻለ ነው ብልጽግና፡፡

የህዝቡን ጥያቄ ለመመለስ የሚያስችል እውነተኛ ፌዴራሊዝም ለመትከል የሰራ፤ ሁሉም በፍትሃዊ መንገድ የሚወከልበትና አካታች ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ለመፍጠርም በትጋት ተንቀሳቅሶ ውጤት ማምጣትም ችሏል፡፡

በኢትዮጵያ ባለፉት አራት ዓመታት ያጋጠሙ በርካታ ፈተናዎችን አልፎ የመጣው ብልጽግና ፈተናዎችን በድል ማለፍ የቻለው አካታችና ሁሉን አቀፍ ህብረ ብሄራዊ ፓርቲ በመሆኑ ነው ፡፡

ኢትዮጵያ ብዙ ቋንቋዎች የሚነገርባት አገር ብትሆንም ሀገራዊ እሴታችንን በአግባቡ መጠቀም ባለመቻላችን የሚገባውን ዕውቅና ሳይሰጣቸው ቀርቷል፡፡

ብልጽግና በህብረ ብሄራዊነት አደረጃጀት አገራዊ ፓርቲ ሆኖ ሲመሰረት በኢትዮጵያ ሁሉንም ቋንቋዎች፣ ባህሎችና እሴቶች ተገቢውን ክብር እንዲሰጣቸው አስችሏል፡፡

አጋር ሲባሉ የነበሩትን ድርጅቶች በማሳተፍ፣ ውሳኔ ሰጭ በማድረግና የተፎካካሪ ፓርቲዎችን ከሚኒስትር ጀምሮ በየደረጃው በማሳተፍ አካታችና ሁሉን አቀፍ መሆኑን በተግባር አሳይቷል፡፡

በሁሉም ልብ ውስጥ ተዳፍና የምትብላላውን ኢትዮጵያ ከፍ አድርጎ ኢትዮጵያውያንን ከጫፍ እስከ ጫፍ ያነቃነቀ፤ የመደመር ፍልስፍናን በማምጣት የኢትዮጵያ ፖለቲካ በይቅርታና መደጋገፍ ላይ ተመስርቶ በሀሳብ ልዕልና እንዲያምን ተግቶ የሰራና የሚሰራ ፓርቲ ነውና፡፡

ብልጽግና ኢትዮጵያዊነትን ከማንነት ጋር አስተሳስሮ የሚያስኬድ፤ ህዝቦች ራሳቸውን በራሳቸው የማስተዳደርና በአስተዳደራቸው ቋንቋቸውን ከመጠቀም ባለፈ ወደ ፌዴራል የማሳደግ እድል የሚሰጥ እና አካታችነቱን በተግባር ማሳዬት የቻለ፤ የጋራ የሆነችውን ኢትዮጵያንም በባለቤትነት ስሜትና በእኩል ተሳትፎ ማልማትና መገንባት እንዲችሉ እየሰራ ያለ፤ ኢትዮጵያዊነትን ከማንነት ጋር አስተሳስሮና አጣጥሞ የሚያስኬድ፤ ሁሉንም ማቀፍ የምትችል፣ኢትዮጵያን ከፖለቲካ ሴራ እና ከመጠላለፍ ጉዞ ለማላቀቅ እየሰራ ያለ፤ በቀጣይም በቁርጠኝነት የሚሰራ ፓርቲ ነው፡፡

•~•~•

"የጎሃ ቃልኪዳናችን የከፍታችን ልክ - ቃላችንን ፈፅመን ከፍታው ላይ እንገናኝ"
•~•~•
ለወቅታዊ ፣ ትክክለኛና አዳዲስ መረጃዎች የፓርቲያችንን የማህበራዊ ገፆች ይወዳጁ።
ትዊተር :- https://twitter.com/AppAmhara?s=09
ዩቲዩብ :- https://youtube.com/channel/UCxQ5MOnm-YH514Qdta0Kysg
ቴሌግራም ፡-https://t.me/appamhara01
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/

መጋቢት 17/2015 ዓ.ምየሕዝብን አንገብጋቢ ችግር ሊፈታ የሚችል የመንገድ ጥገና በመካሄድ ላይ ነው።የሰከላ ወረዳ መንገድ እና ትራንስፖርት ጽ/ቤት በ2015 በጀት ዓመት በእቅድ ከያዛቸው የ...
26/03/2023

መጋቢት 17/2015 ዓ.ም
የሕዝብን አንገብጋቢ ችግር ሊፈታ የሚችል የመንገድ ጥገና በመካሄድ ላይ ነው።
የሰከላ ወረዳ መንገድ እና ትራንስፖርት ጽ/ቤት በ2015 በጀት ዓመት በእቅድ ከያዛቸው የመንገድ ጥገና ፕሮጀክቶች አንዱ የሆነው ከግሽ ዐባይ-ዘገዛ-አሰዋ የመንገድ ጥገና ፕሮጀክት በፍጥነት እየተሠራ ነው። መንገድ የሀገርም ሆነ የአካባቢን የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካ እና የማኅበራዊ ክንዋኔዎች ጤናማ እንዲሆኑ የሚጫወተው ሚና እጅግ የጎላ ነው።
==========================
በዚህ መሠረት መ/ቤታችን በበጀት ዓመቱ ከመንግሥት እና ከኅብረተሰቡ ተሳትፎ በሚሰበሰብ የገንዘብ መዋጮ ሁለት መንገዶችን ለመጠገን አቅዶ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን ሲያካሂድ ከቆየ በኋላ ከየካቲት 23/2015 ዓ.ም ጀምሮ በመጀመሪያው ዙር የተጀመረው የመንገድ ጥገና በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል።
==========================
ይህ መንገድ የሰከላ ወረዳን ከአጎራባች ወረዳ ጃቢ ጣናን ጋር የሚያገናኝ ሲሆን የጥገና ሥራው ሙሉ ወጭ በወረዳው መንግሥት በተበጀተ በጀት ነው። ቀሪ የአራት ኪሎ ሜትር የሰከላና ጃቢ ጠናን ወረዳን የሚያስተሳስር የመንገድ የጠረጋና የጠጠር ማልበስ ሥራ ደግሞ በኅብረተሰቡ የገንዘብ መዋጮ የሚከናወን ይሆናል። ለዚህ የመሠረተ ልማት መሳካት ከጎናችን ሆናችሁ የኅብረተሰብ ንቅናቄ የምታፋጥኑ አስተባባሪ ኮሚቴዎች እና በገንዘብ እና በሐሳብ ለምትደግፉን ባለድርሻ አካላት ምስጋናችን የላቀ ነው። ተቋርጦ የነበረው የተሽከርካሪ ስምሪትም አገልግሎት መስጠት የጀመረ መሆኑን ስናበስር በታላቅ ደስታ ነው!!!
==≥=========
መጋቢት 2015
ግሽ ዐባይ

26/03/2023

በጠንካራ አንድነት ጠንካራ መሪ ይወለዳል!

ያለንበት ሁኔታ እጅግ ተለዋዋጭ ውስብስብ ማህበራዊ፣ ፖለቲካል-ኢኮኖሚ ችግሮች ያሉበት ግን ደግሞ በሕብረት መቆም እስከቻልን ድረስ አቅማችን ከችግሮቻችን በላይ ማድረግ የምንችልበት ነው።

ካለንበት ውስብስብ ችግር በድል ለመውጣት ብቸኛው መንገድ በችግሮቻችን ምልከታ ላይ የጋራ አረዳድ መፍጠር፣ መፍትሔ ለመስራት አቅምን ማሰባሰብ ይጠበቅብናል። የተበተነ አቅም ከጥቅሙ ኪሳራው ያመዝናል። ለዚህ ደግሞ ጠንካራ አንድነት ቀዳሚው እርምጃ ነው።

ከመግባባት ባለፈ ፈተናዎችን ለማለፍ ያስችላል ተብለው ለተቀመጡ መፍተሔዎች ወደ ተግባር እንዲቀየሩ የሕዝብ፣ የመንግስትና የፓርቲ አደረጃጀቶች በጋራ መትጋት አለባቸው፡፡

ታሪክ አንድነት እና ድል አንድ መሆናቸውን በተግባር አስረድቶናል፡፡ አያት ቅድመ አያቶቻችን የትኛውም ዓይነት ህዝባዊ ድሎችና የልማት ውጤቶች ስኬትን የተጎናፀፉት በጠነከረ ህብረትና አንድነት መሆኑ ከታሪክ ገፆች ተምረናል። ይህ የኛ ዘመን ነው፤ ታሪክ የምናስተምርበት ብቻ ሳይሆን የዘመናችንን ገድል የምንሰራበት ሊሆን ይገባል።

አንድነት ሃይል ነው፣ እናም ልዩነቶቻችንን ወደ ጎን ትተን በሙሉ ኃይላችን ለጋራ አላማችን አሸናፊነት እንድንነሳና ለእውነተኛ ወንድማማችነት እና አንድነት ልንታገል ይገባል። ይህ የወረስነው ታሪክ ስለሆነ ብቻ ሳይሆን የዘመኑ መንፈስም ይህን ያስገድዳል። እውነት ነውና።

ይህን የድላችንን ስኬት ጊዜ ወስደው ያጠኑት የውጭ ኃይሎች ለአንድነት ጥንካሬ ማፍረሻ ይሆን ዘንድ እርስ በእርስ በመለያየት ፕሮጀክት ሊያሸንፉን እየጣሩ እንደሚገኙም እሙን ነው፡፡ በውጭ ኃይሎች ቀጥተኛ ተሳትፎ አንድነትን በሚጠበቀው ልክ ማፍረስ ሲሳናቸውም በውስጥ ተከፋይና የሥልጣን ጥመኛ በሆኑ የእናት ጡት ነካሽ ባንዳዎች አማካኝነት የሕዝብ፣ የመንግሥትና የፓርቲን መስተጋብር በሚንድ አልፎም የውስጥ አንድነትን በሚያፈርስ መልኩ መርዛቸውን ሲረጩ፤ የለውጥ ተስፋችንን ሊያጨልሙ ላይና ታች ቢሉም በሕዝባችን ብልህነት፣ በአመራሩ አርቆ አሳቢነት ወጥመዱ ውስጥ አልወደቅንም።

ይህም ሆኖ የውስጥና የውጭ ጠላቶቻችን ዛሬም በቀቢፀ ተስፋ ውስጥ ሆነው ከሚዲያ ዘመቻ ጀምሮ በተግባር እየተገለጠ የጥፋት ተልዕኳቸው ላይ እንደተጣዱ ነው።

አንዱ አካባቢ በሌላው ላይ ብቻ ሳይሆን ወንድም በወንድሙ ላይ ሾተላይ እንዲመዝ የሚያደርግ የጥፋት ፕሮጀክት ተሰርቶ እየተተገበረ ነው፡፡ አንዱ ሲለማ ሌላው የጦርነት ነጋሪት እንዲጎስም የሚያደርገው ይኸው ፕሮጀክት ነገ የፕሮጀክቱን ጠንሻሽ አካል እንደሚያጠፋ ለመረዳት ያልፈለገው ይኸው አካል ጠላት ብሎ በፈረጀው አካል ላይ ስኬቱን ለማየትና በሞት ለመሳለቅ ጊዜ አጥሮት ነው፡፡

ሁኔታዎችን አስፍቶ ማስተዋል ካልተቻለ ወጥመዱ ብዙ ነው። በመሪህ ላይ ጣትህን በመቀሰር፣ ሰፈር ለይቶ ለጥልና ለቁርሾ መጣደፍ የሁኔታ ግምገማ ጎደሎነት ነው። ስለሆነም ለእኩይ ዓላማ ስኬት መሳሪያ ከመሆን እንቆጠብ፡፡

ምሁራን ፖለቲከኛውን፣ ፖለቲከኛው ምሁሩን፣ የንግዱ ማህበረሰብ ህዝቡንም ሆነ ፖለቲከኛውን እንዲሁም ህዝቡ መሪው ላይ ጣቱን ከመቀሰር ይውጣና በአንድነት፤ ለአንድነት ይነሳ!!!

የኛም ሆነ የዓለም ታሪክ ደጋግሞ እንዳስረዳን በጠንካራ አንድነት ውስጥ ጠንካራ መሪ ይወለዳል! ይህ ሂደት ደግሞ ያሉህን መሪዎች በመጠበቅ ውስጥ የሚሆን (ጀግና መፍጠር) ነው።

Address

Sekela
Sekela Gish Abay

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Sekela woreda Road and Transport Office Cell posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share