28/02/2025
በቤንች ሸኮ ዞን ትራንስፖርት እና መንገድ ልማት መምሪያ በደቡብ ቤንች ወረዳ ውስጥ ያሉ የመንገድ ልማት ስራዎችን ገበኘ።
የካቲት 21/2017ዓ.ም ደ/ወርቅ: በቤንች ሸኮ ዞን ትራንስፖርት እና መንገድ ልማት መምሪያ ሀላፊ አቶ አበበ ኑራ የተመራ ቡንድን በደቡብ ቤንች ወረዳ ውስጥ የተሰሩ ያሉ አጠቃላይ የመንገድ ልማት ስራዎች ላይ ምልከታ አድርጓል ።
በመንገድ ልማት ስራዎች ከወረዳው ደ/ወርቅ ከተማ እስከ ጊጪ ያለው 19ኪ.ሜ የመንገድ ጥገና ስራዎች ፣ ጃንቹ ቀበሌን ከአይናምባ ቀበሌ የሚያገናኘውና በመገንባት ላይ ያለው የዛን ወንዝ ድልድይ እና በክልል ገጠር መንገድ በጀት ግንባታው ተጀምሮ የተቋረጠው የጌዱ ቀበሌ ዚብን ወንዝ ድልድይ ግንባታ ላይም ምልከታ ተደርጓል ።
በምልከታው ላይ የቤንች ሸኮ ዞን ትራንስፖርት እና መንገድ ልማት መምሪያ ሀላፊ አቶ አበበ ኑራ እና የወረዳው ትራንስፖርት እና መንገድ ልማት ጽ/ቤት ተወካይ ሀላፊ አቶ ሰለሞን ጸሀፊን ጨምሮ የዞን እና የወረዳው ትራንስፖርት እና መንገድ ልማት ተቋማት ባለሞያዎ ተገኝተዋል ።
ወረዳው በመንግሥት እና በህብረተሰቡ ተሳትፎ ትልቅ በጀት መድቦ ሰፊ የመንገድ ጥገና እና ከፈታ ስራዎች ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ መገኘቱ የሚደነቅ መሆኑን የቤንች ሸኮ ዞን ትራንስፖርት እና መንገድ ልማት መምሪያ ሀላፊ አቶ አበበ ኑራ በጉብኝቱ ወቅት ተናግረዋል ።
የመምሪያ ሀላፊው አክለውም በወረዳው ውስጥ በተለያዩ የበጀት ምንጮች እየተሰሩ የቆሙ የመንገድ ጥገና እና ድልድይ ግንባታዎች ተጠናቀው አገልግሎት እንዲሰጡ ከሚመለከታቸው አካላት ተነጋግሮ እልባት እንዲያገኙ የማድረጉ ስራ እና የዞኑም ድጋፍና ክትትል ተግባርም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል ።
የወረዳው ትራንስፖርት እና መንገድ ልማት ጽ/ቤት ተወካይ ሀላፊ አቶ ሰለሞን ጸሀፊ በበኩላቸው በዞኑ ትራንስፖርት እና መንገድ ልማት መምሪያ ባለድርሻ አካላት በምልከታው ወቅት መሻሻል አለባቸው ተብለው የተሰጡትን ግብረ መልሶች ተቀብለው ተግባራዊ ለማድረግ ከመቼውም ጊዜ በላይ በትኩረት እንደሚሰራ ገልጸዋል ።
ምንጭ:- ደቡብ ቤንች ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት