Asatco Customs Clearing Agent

Asatco Customs Clearing Agent ☆ Customs clearing service and consultancy for all kinds of import and export businesses.

ላልተወሰነ ጊዜ የውጭ ምንዛሬ የማይፈቀድላቸው ከውጭ የሚገቡ ዕቃዎች ዝርዝር ላይ ማሻሻያ ተደረገ ህዳር 9 / 2015 ዓ.ም - ከዚህ ቀደም ላልተወሰነ ጊዜ ተላልፎ በነበረው የውጭ ምንዛሬ የማ...
25/12/2022

ላልተወሰነ ጊዜ የውጭ ምንዛሬ የማይፈቀድላቸው ከውጭ የሚገቡ ዕቃዎች ዝርዝር ላይ ማሻሻያ ተደረገ
ህዳር 9 / 2015 ዓ.ም - ከዚህ ቀደም ላልተወሰነ ጊዜ ተላልፎ በነበረው የውጭ ምንዛሬ የማይፈቀድላቸው ከውጭ የሚገቡ እቃዎች ዝርዝር ላይ ማሻሻያ ማድግ በማስፈለጉ ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ዕቃዎች ላይ ማሻሻያ መደረጉን የገንዘብ ሚኒስቴር ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክና ለጉምሩክ ኮሚሽን በጻፈው ደብዳቤ አሳውቋል፡፡
ማሻሻያ የተደረገባቸው ከውጭ የሚገቡ እቃዎች የሚከተሉት ናቸው
1. በታሪፍ ቁጥር 9401. 9000 እና 9403. 9000 የሚመደቡ እቃዎች ክፍሎች ማምረቻ ግብአቶች፣
2. ምርቶቻቸውንና አገልግሎቶቻቸውን በውጭ ምንዛሬ የመሸጥ ፍቃድ ያላቸው ሬስቶራንቶችና ሱፐር ማርኬቶች የራሳቸውን የውጭ ምንዛሬ ተጠቅመው የሚያስገቧቸው ዕቃዎች፣
3. ባለ ኮከብ ሆቴሎች የራሳቸውን የውጭ ምንዛሬ ተጠቅመው የሚያስመጧቸው ዕቃዎችና
4. የቀረጥ ነጻ ሱቆች የሚያስመጧቸው ዕቃዎች
የውጭ ምንዛሬ ክልከላው የማይመለከታቸው መሆኑ ተገልጽዋል፡፡
ላልተወሰነ ጊዜ የውጭ ምንዛሬ የማይፈቀድላቸው ከውጭ የሚገቡ የ38 እቃዎች ዝርዝር በጥቅምት ወር 2015 ዓ.ም ይፋ መደረጉ ይታወሳል፡፡

⚜የውጭ ፍተሻ የሚፈቀድላቸው ድርጅቶች እና ዕቃዎች ጋር በተያያዘ የተደረገውን ማስተካከያ በተመለከተ  10/03/2015 የተላለፈ ሠርኩላር ⚜New Site Inspection Permit Amend...
25/12/2022

⚜የውጭ ፍተሻ የሚፈቀድላቸው ድርጅቶች እና ዕቃዎች ጋር በተያያዘ የተደረገውን ማስተካከያ በተመለከተ 10/03/2015 የተላለፈ ሠርኩላር

⚜New Site Inspection Permit Amendments Circular Issued on November 12/2022

ጅግጅጋ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ግምታዊ ዋጋው 27 ሚሊዮን ብር የሆነ አንደኛ ደረጃ   እርጥብ ጫት በቁጥጥር ስር ዋለ ********************************************...
17/12/2022

ጅግጅጋ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ግምታዊ ዋጋው 27 ሚሊዮን ብር የሆነ አንደኛ ደረጃ እርጥብ ጫት በቁጥጥር ስር ዋለ ***********************************
***********************************

ታህሳስ 04 ቀን 2015 ዓ.ም ( ሃያ ሰባት ሚሊዮን ብር የሆነ እርጥብ ጫት ጅግጅጋ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አማካኝነት በቁጥጥር ስር ውሏል፡

ግምታዊ ዋጋዉ አስራ አምስት ሚሊየን ብር የሆነ አንደኛ ደረጃ እርጥብ ጫት በህገወጥ መንገድ ከሀገር ለመዉጣት በሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3-67295 ኦሮ እና ኮድ 3-05474 ድሬ የሆኑ አይሱዙ ተሽከርካሪዎች ተጭኖ በጫካ ለመዉጣት ሲሉ እንዲሁም ግምታዊ ዋጋዉ አስራ ሁለት ሚሊየን ብር የሆነ አንደኛ ደረጃ እርጥብ ጫት በህገ ወጥ መንገድ ከሀገር ሊወጣ ሲል በቶጎ ጫሌ መቆጣጠሪያ ጣቢያ ሰራተኞች ፣ በፌዴራል ፖሊስ አባላት ፣ በክልሉ ሚሊሻዎችና በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የኮንትሮባንድ ክትትል ሠራተኞች በተደረገ ጥብቅ ክትትል በቁጥጥር ስር ማዋል ተችሏል፡፡
በዚህ ስራ ላይ ተሳትፎ ላደረጉ ለቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ አመራሮች እና ሰራተኞች ፌዴራል ፖሊስ አባላትና የክልሉ ሚሊሻዎች የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ምስጋናውን ያደርሳል፡፡
ኮንትሮባንድ እና ህገወጥ ንግድ የአፈጻጸም ስልቱ ተለዋዋጭ በመሆኑ ድርጊቱን ለመግታትና በሀገር ኢኮኖሚ የሚያሳድረውን አሉታዊ ተጽእኖ ለመከላከል ጉምሩክ ኮሚሽን ብቻ የሚያደርገው እንቅስቃሴ በቂ ባለመሆኑ ሁሉም ባላድርሻ አካላትና ህብረተሰቡ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ የጉምሩክ ኮሚሽን ጥሪውን ያቀርባል፡፡
ጉምሩክ ኮሚሽንን የተመለከቱ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/asatco99
በድረ ገጽ፦ www.business.site.asatco
በቴሌግራም፦ https://t.me/asatco99

ጅግጅጋ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት  ግምታዊ ዋጋው 5 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር  የሆነ እርጥብ ጫት በቁጥጥር ስር ዋለ***********************************በጅግጅጋ ጉምሩክ ቅርን...
11/12/2022

ጅግጅጋ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ግምታዊ ዋጋው 5 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር የሆነ እርጥብ ጫት በቁጥጥር ስር ዋለ
***********************************
በጅግጅጋ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ህዳር 29 ቀን 2015 ዓ.ም ግምታዊ ዋጋው 5 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር የሆነ እርጥብ ጫት በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡

ወደ ጎረቤት ሀገራት በህገወጥ መንገድ ሊወጣ ሲል የተያዘው እርጥብ ጫት፣ በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የኢንተለጀንስ ባለሙያዎች እና የኮንትሮባንድ መከላከል ሠራተኞች በጋራ ባደረጉት ጥብቅ ክትትል በቁጥጥር ስር ማዋል ተችሏል፡፡
በዚህ ስራ ላይ ተሳትፎ ላደረጉ ለቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ አመራሮች እና ሰራተኞች የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ምስጋናውን ያደርሳል፡፡
ኮንትሮባንድ እና ህገወጥ ንግድ የአፈጻጸም ስልቱ ተለዋዋጭ በመሆኑ ድርጊቱን ለመግታትና በሀገር ኢኮኖሚ የሚያሳድረውን አሉታዊ ተጽእኖ ለመከላከል ጉምሩክ ኮሚሽን ብቻ የሚያደርገው እንቅስቃሴ በቂ ባለመሆኑ ሁሉም ባላድርሻ አካላትና ህብረተሰቡ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ የጉምሩክ ኮሚሽን ጥሪውን ያቀርባል፡፡
ጉምሩክ ኮሚሽንን የተመለከቱ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/asatco99
በድረ ገጽ፦ www.business.site.asatco
በቴሌግራም፦ https://t.me/asatco99

August 2022_የታሪፍ ማሻሻያ  ሠርኩላር
11/12/2022

August 2022_የታሪፍ ማሻሻያ ሠርኩላር

December 2022 የታሪፍ ማሻሻያ  ሠርኩላር
10/12/2022

December 2022 የታሪፍ ማሻሻያ ሠርኩላር

To chat exporters: Fob Price for chat exported to Somalia
10/12/2022

To chat exporters: Fob Price for chat exported to Somalia

December 2022_ወቅታዊ_የባህር _ትራንስፖርት_ማጓጓዣ_ዋጋ_መረጃ
09/12/2022

December 2022_ወቅታዊ_የባህር _ትራንስፖርት_ማጓጓዣ_ዋጋ_መረጃ

03/12/2022

የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን እና የንግድ እና ቀጣናዊ ትሥሥር ሚኒስቴር እና በኮንትሮባንድ እና ሕገ-ወጥ ንግድ ላይ የሚሳተፉ ሕገ-ወጦችን ላይ ሕጋዊ እርምጃ መውሰድ የሚያስችል የውሳኔ ሀሳብ
**********************************************
የኮንትሮባንድ እና ሕገ ወጥ ንግድ መከላከል እና ቁጥጥርን አስመልክቶ የንግድ እና ቀጣናዊ ትሥሥር ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን በጋራ የሰጡት ሙሉ መግለጫ እንደሚከተለው ቀርቧል፦
ሕገ-ወጥነት እና ሕገ-ወጦች ላይ ተከታታይ ሕጋዊ እርምጃዎችን በመውሰድ ችግሩን ለመግታት እና የተሳለጠ የወጪ ንግድ ሥርዓት እንዲኖር በማድረግ የሀገራችንን ብልፅግና ለማረጋገጥ መንግሥት ልዩ ክትትል እያደረገ የሚገኝ ሲሆን በዚህም መነሻነት በንግድ እና ቀጣናዊ ትሥሥር ሚኒስቴር እና በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን መካከል በጉዳዩ ዙሪያ ጥልቅ ውይይት ከተደረገ በኋላ የሚከተሉት ውሳኔዎች ተላልፈዋል።

1ኛ. ማንኛውም ግለሰብ፣ የንግድ ድርጅት፣ የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ተቋም ወይም ኩባንያ የወጪ ንግድ ምርቶችን ይዞ በሚንቀሳቀስበት ወቅት ምርቶቹ ለውጪ ገበያ የሚቀርቡ መሆናቸውን እና የላኪውን ሕጋዊነት የሚያረጋግጥ የወጪ ንግድ የመላኪያ ፈቃድ (Export permit) እና ሌሎች ለወጪ ንግድ የሚጠየቁ ሰነዶችን ሳይይዝ እንዲሁም የምርት አስተሸሸግና ሌብሊንግ (Export packaging and product labelling)፣ ምርቱ ላይ ሳይኖር የጉምሩክ ኬላዎችን አቋርጦ ማለፍ በጥብቅ የተከለከለ ነው።

በመሆኑም የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ተቋማትም የጭነት አገልግሎት ከመስጠታቸው በፊት እነኚሀን ሕጋዊ ዶክመንቶች በመጠየቅ አገልግሎት እንዲሰጡ ጥብቅ ማሳሳቢያ የተሰጠ ሲሆን ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች ሳያሟላ ወይም መሟላታቸውን ሳያረጋግጥ በጉምሩክ ኬላዎችም ይሁን ከኬላዎች ውጪ በሚደረጉ ፍተሻዎች ከተያዘ ወይም ማናቸውንም ሕጋዊ አሠራሮችን በማያከብሩ አካላት ላይ ሕጋዊ እርምጃ የሚወሰድ ይሆናል።

2ኛ. የኢፌዴሪ ሕገ-መንግሥት አንቀፅ 55(2-ለ) 'በክልሎች መካከል የሚኖር የንግድ ልውውጥ እንዲሁም የውጭ ንግድ ግንኙነትን በተመለከተ' የኢፌዴሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሥልጣን እና ተግባር መሆኑን በግልጽ ተደንግጓል። በዚሁ መሠረት የአስፈጻሚ አካላትን ተግባር እና ኃላፊነት ለመወሰን የወጣው አዋጅ ቁጥር 1263/2014 አንቀጽ 22 መሠረት በንግድ እና ቀጣናዊ ትሥሥር ሚኒስቴር ከሚሰጥ የወጪ ምርት መላኪያ ፍቃድ ውጪ በክልሎች አስፈፃሚ አካላት የሚሰጡ ፍቃዶች፣ መሸኛዎች እንዲሁም ሌሎች የይለፍ ማስረጃዎች ተቀባይነት የላቸውም ብቻ ሳይሆን ነጋዴዎችንም ተጠያቂ እንዲሆኑ የሚያደርጉ በመሆኑ የክልል አስፈፃሚ አካላት ከላይ የተገለጹትን ማስረጃዎች እንዳይሰጡ ውሳኔ ተላልፏል።

በመሆኑም ነጋዴዎች በክልል አስፈፃሚ አካላት የሚሰጡ ማስረጃዎችን አቅርበው መስተናገድ የማይችሉ ሲሆን ይህንን ተላልፈው በሚገኙ አካላት ላይ የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽንን ተግባር ኃላፊነት እና አደረጃጀት ለመወሰን በወጣው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 437/2011 መሠረት ዕቃው የኮንትሮባንድ ዕቃ እንደሆነ ተቆጥሮ ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድ አውቀው ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ውሳኔ ተላልፏል።

3ኛ. የዚህን ሥራ አፈፃፀም ለመከታተል ከንግድ እና ቀጣናዊ ትሥሥር ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን እንዲሁም ከኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ የኦፕሬሽን ቡድን በተቋቋመ ግብረ-ኃይል በሀገሪቱ የተለያዩ ቦታዎች ተሰማርቶ አስፈላጊውን ሕጋዊ እርምጃ እንዲወስድ ተወስኗል።
ይህ ውሳኔ አገሪቱ ካሉባት ተደጋጋሚ ተግዳሮቶች በጽናት እየወጣች ወደ ከፍታዋ ማማ የምታደርገውን ጉዞ በከፍተኛ ሁኔታ የሚያጠናክር መሆኑ ታውቆ ኅብረተሰቡ ወንጀለኞችን በማጋለጥ እንዲተባበር እና ከመንግሥት ጎን እንዲቆም ጥሪ ቀርቧል።

ጉምሩክ ኮሚሽንን የተመለከቱ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/asatco99
በድረ ገጽ፦ www.asatco.business.site
በቴሌግራም፦ https://t.me/asatco99

Ethiopian Customs Is Responsible for Import and Export Goods.
With this page we will share information about customs.

N.B: To chemical Importers for Industries and other sectors.
28/11/2022

N.B: To chemical Importers for Industries and other sectors.

⚜አዲሱ_ ወደ አገር በሚገቡ እቃዎች ላይ የማህበራዊ ልማት ቀረጥ ለማስከፈል የወጣ ደንብ ቁጥር 519_2014⚜New _Social Welfare Levy on Imported Goods  Regulat...
24/11/2022

⚜አዲሱ_ ወደ አገር በሚገቡ እቃዎች ላይ የማህበራዊ ልማት ቀረጥ ለማስከፈል የወጣ ደንብ ቁጥር 519_2014

⚜New _Social Welfare Levy on Imported Goods Regulation No.519_2022

⚠This New Regulation is Effective from 6th August; 2022

Address

Nib Insurance Building, 2nd Floor, Room Number 203
Dire Dawa

Opening Hours

Monday 07:30 - 12:00
14:30 - 18:00
Tuesday 07:30 - 12:00
14:30 - 18:00
Wednesday 07:30 - 12:00
14:30 - 18:00
Thursday 07:30 - 12:00
14:30 - 18:00
Friday 07:30 - 12:00
14:30 - 18:00
Saturday 07:30 - 12:00

Telephone

+251703756569

Website

https://asatco.business.site/

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Asatco Customs Clearing Agent posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Asatco Customs Clearing Agent:

Share