30/07/2026
የአዴት ቴ/ሙ/ማ/ኮሌጅ የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሥራን አከናወነ ።
ሐምሌ 23/2018 ዓ.ም
በሰሜን ጎጃም ዞን በአዴት ከተማ አስተዳደር የአዴት ቴ/ሙ/ማ/ኮሌጅ 3 የአረጋዊያን እና አቅመ ደካማ ቤት በማደስ የበጎነት ተግባራት ሥራን አከናወነ ።
ኮሌጁ 3ቱንም የአቅመ ደካሞች ቤት ከአዴት ከተማ አስተዳደር ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ጋር በመነጋገር ተረክቦ ከ 55 ሽህ ብር በላይ ወጭ አውጥቶ በኮሌጁ ሙያተኞች እና ሰራተኞች ጉልበት ወጭ የተሸፈነው ይህ ሰብዓዊ ተግባር 3 ቱንም ቤቶች ሙሉ እድሳት አድርጎ ሰርቶ ያስረከበ ሲሆን
በዚህም የበጎነት ተግባር ላይ የኮሌጁ ዲንዎች እና ሠራተኞች በሥራው ላይ በመገኘት በሙያቸውና በጉልበታቸው ለበጎነት ተግባር በመስራታቸውና ላበረከቱት ሰብዓዊ ተግባር ደስተኞች መሆናቸውን በመግለፅ ይህ ማህበረሰብ ተኮር የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሥራ ለተቸገሩ ወገኖች ጋን በጠጠር ይደገፋል እንደሚባለው የማኅበረሰቡን የእርስ በርስ የመረዳዳትና የመደጋገፍ ባህልን እንደሚያጠናክርም ገልፀዋል ።