02/06/2026
#የተሟላ ግልጋሎት ለመሰጠት በሰሚት #
(ሲቲ ባስ ግንቦት 23 ቀን 2018 ዓ.ም) የአዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት የሰሚት ቅርንጫፍ የመማክርት ጉባኤ አባላት ከቅርንጫፉ ዋና ስራ አስፈፃሚዎችና በየደረጃው ካሉ የስራ መሪዎች ጋር እየተከናወኑ የሚገኙ አገልግሎቶች ምን እንደሚመስሉ ውይይትና ግምገማ ተካሄደ፡፡
የትራንስፖርት እጥረትና የአገልግሎት አሰጣጥ መስተጓጎል እንዳይፈጠር የአውቶቡሶቻችን እንቅስቃሴ በተመደቡበት መስመር የአገልግሎት አሰጣጡ ምን እንደሚመስል ተነጋግረን የመፍትሄ እቅጣጫዎችን አስቀምጠን እንወያያለን ሲሉ የመማክርት ጉባኤው ዋና ሰብሳቢ አቶ ማርቆስ ለማ ተናግረዋል።
የሰሚት ቅርንጫፍ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ደሱ አሰፋ እንዳሉት ስራዎችን በጋራ ተነጋግሮና ተባብሮ መስራት ለኛ ትልቅ አቅም ይፈጥርልናል ከመማክርት ጉባኤው ጋር በርካታ ስራዎችን በመስራት ውጤት ያመጡ ክንውኖች ከመፈጠራቸው ባሻገር ለቀጣይም ይበል የሚያሰኝ ነው ብለዋል ። አያይዘውም ቅርንጫፋችን በጋራ መኖሪያ አካባቢ እንደመሆኑ መጠን ፍሰቱ ስለሚበዛ ህብረተሰቡ በጠየቀን ጥያቄ መሰረት ችግሮችን ለመፍታት ትልቅ እርብርብ አድርገን ለማህበረሰቡ ምላሽ በመስጠት ማህበረሰቡም ከኛ ጋር በመሆን አብሮነታቸውን አሳይተውናል ብለዋል ።
በውይይቱ ወቅት በቅያሬ ሰአት የሚነሱ ጥያቄዎችን በተገቢው መንገድ ክትትል በማድረግ ቁጥጥሩን በማጠናከር የትራንስፖርት ጥያቄዎቹ የተፈቱበት ሁኔታ መፈጠሩ ተነስቷል ፡፡ እንዲሁም የትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጠን ለማሳለጥ በጋራ እየተሰራ መሆኑን ሁሉም አካል ይገነዘባል በመሆኑም በቀጣይ ይህን አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል በማለት በውይይቱ ወቅት መገባባት ላይ ተደርሷል፡፡
እንዲሁም ከመድረኩና ከቤቱ በተነሱ ሃሳቦና ጥያቄዎች መሰረት የቅርንጫፉ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ደሱ አሰፋ ማብራሪያና ምልሽ ሰተዋል ፡፡ በመጨረሻም የመማክርት ጉባኤ አባላቶች ቅርንጫፍ ፅ/ቤቱ ውስጥ የተሰሩ በርካታ ስራዎችንና የሌማት ትሩፋቶችን በመዘዋወር ጉብኝት አድርገዋል ፡፡