Ethio-Transport and Logistics International Exhibition

Ethio-Transport and Logistics International Exhibition The first international business exhibition on transport and logistics in Ethiopia.

The exhibition will be a stage for all transporters & their service providers, all logistics and supply-chain operators and all manufacturers, assemblers, exporters, and importers of trucks, buses, vehicle, motorized & non-motorized bikes and their parts.

"እንኳን አደረሳችሁ!"ዒድ ሙባረክ !!!
30/04/2022

"እንኳን አደረሳችሁ!"
ዒድ ሙባረክ !!!

መልካም የፋሲካ በዓል ይሁንላችሁ!
23/04/2022

መልካም የፋሲካ በዓል ይሁንላችሁ!

መልካም የስቅለት በዓል!
22/04/2022

መልካም የስቅለት በዓል!

ስማርት ማኔጅመንት ሰርቪስስ የግብርና መሣሪያዎችን ለከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ዑማ አስረከበ!ስማርት ማኔጅመንት ሰርቪስስ፣ ከኮቪድ-19 (ኮሮና ቫይረስ) ወረርሽኝ ጋር ተያይዞ፣ በአዲስ አበባ ከ...
15/05/2020

ስማርት ማኔጅመንት ሰርቪስስ የግብርና መሣሪያዎችን ለከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ዑማ አስረከበ!

ስማርት ማኔጅመንት ሰርቪስስ፣ ከኮቪድ-19 (ኮሮና ቫይረስ) ወረርሽኝ ጋር ተያይዞ፣ በአዲስ አበባ ከተማ ሊከሰት የሚችለውን የምግብ ዕጥረት ቀድሞ ለመከላከል እንዲቻል በማሰብ፣ የከተማ አስተዳደሩ ለጀመረው የከተማ ግብርና መርሃ ግብር ከፍተኛ ዕገዛ ያላቸውን የግብርና መሣሪያዎች፣ ለከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ኢ/ር ታከለ ዑማ አስረከበ፡፡
ከንቲባው ኢ/ር ታከለ ዑማ፣ ዛሬ ዓርብ (ግንቦት 7/2012) ጎሮ በሚገኘው አይሲቲ ፓርክ (ICT park) ተገኝተው፣ በአዲስ አበባ ከተማ የግብርና ስራውን ለሚያከናውኑ አርሶ አደሮች ልዩ ልዩ ለግብርና ስራ የሚያስፈልጉ መሣሪያዎችን የሰጡ ሲሆን፣ በዚሁ ፕሮግራም ላይ የስማርት ማኔጅመንት ሰርቪስስ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶክተር አዲል አብደላ፣ መርሃ ግብሩን ለማገዝ የላቀ ድርሻ አላቸው የተባሉትን የግብርና እጅ መሳሪያዎች ለክቡር ከንቲባው አስረክበዋል፡፡
ስማርት ማኔጅመንት ሰርቪስስ እና ሌሎችም የከተማዋ ባለሃብቶች ይህን መርሃ ግብር ለማገዝ ላደረጉት ድጋፍ ምስጋናቸውን ያቀረቡት ከንቲባው፣ የግብርና መሣሪያዎቹ ከተማዋ በምግብ ራሷን ለመቻል ለምታደርገው ጥረት ከፍተኛ ጉልበት እንደሚፈጥሩ ተናግረዋል፡፡
የስማርት ማኔጅመንት ሰርቪስስ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶክተር አዲል አብደላ በበኩላቸው፣ የከተማ ግብርና እንዲስፋፋ የከተማ አስተዳደሩ የሚያደርገውን ጥረት ለመደረፍ የግብርና መሳሪያዎቹ በከፍተኛ የገንዘብ ወጪ የተገዙ መሆናቸውን ገልጸው፣ በዚህ ጊዜ እንዲህ ባለው የጋራ ጉዳይ በህብረት መቆም የውዴታ ብቻ ሳይሆን የዜግነት ግዴታ ጭምር መሆኑን አመልክተዋል፡፡

የፆም ወቅትን በሩሚ በርገር!ሩሚ በርገር ፆሙን ታሳቢ ያደረጉ ጣፋጭ የፆም ምግቦችን አዘጋጅቶ ይጠብቃችኋል፡፡አትላስ አካባቢ፣ ፒያሳ ኤሊያና ሞል፣ ብስራተ ገብርኤል፣ ለቡ፣ ሰሚትና ቤቴል ከሚገ...
11/03/2020

የፆም ወቅትን በሩሚ በርገር!
ሩሚ በርገር ፆሙን ታሳቢ ያደረጉ ጣፋጭ የፆም ምግቦችን አዘጋጅቶ ይጠብቃችኋል፡፡
አትላስ አካባቢ፣ ፒያሳ ኤሊያና ሞል፣ ብስራተ ገብርኤል፣ ለቡ፣ ሰሚትና ቤቴል ከሚገኙት ስድስቱ የሩሚ በርገር ቅርንጫፎች ወደ አንዱ ጎራ ብለው ቬጅ በርገር፣ ቬጅ ፒዛ፣ ቱና በርገር፣ ቱና ፒዛ፣ ፊሽ በርገር፣ ፊሽ ሳንድዊችና ሚክስድ ሳላድን የመሳሰሉ ጣፋጭ ምግቦችን እንዲሁም ልዩልዩ ጣዕም ያላቸው ጁሶችን ማዘዝ ይችላሉ፡፡
የሩሚ በርገር ሰባተኛው ቅርንጫፍ በቦሌ መድኃኔዓለም አካባቢ (ዩጎ ሲቲ ቸርች ፊት ለፊት) በቅርቡ ስራ ይጀምራል፡፡

የስማርት ማኔጅመንት ሰርቪስስ ዋና ስራ አስፈጻሚ የስራ አቅጣጫ ሰጡ!የስማርት ማኔጅመንት ሰርቪስስ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር አዲል አብደላ የካቲት 19/2012 ዓ.ም ከስማርት እህት ኩባኒያዎች...
27/02/2020

የስማርት ማኔጅመንት ሰርቪስስ ዋና ስራ አስፈጻሚ የስራ አቅጣጫ ሰጡ!

የስማርት ማኔጅመንት ሰርቪስስ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር አዲል አብደላ የካቲት 19/2012 ዓ.ም ከስማርት እህት ኩባኒያዎች የስራ ሃላፊዎች ጋር በስማርት ዋና መ/ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ ባደረጉት ስብሰባ ድርጅቶቹ በበጀት ዓመቱ ያለፉት 6 ወራት ያሳዩትን የስራ አፈጻጸም ገምግመው ለቀጣይ 6 ወራት መከተል ያለባቸውን አቅጣጫ አመላክተዋል፡፡
በዚሁ ስብሰባ “ሃገራችን አሁን ያለችበት ወቅታዊ ሁኔታ በተለይ በንግዱ ዓለም ለተሰማሩ እጅግ አስቸጋሪና ህልውናን እስከመፈታተን የደረሰ ሆኗል” ያሉት ዋና ስራ አስፈጻሚው ዶ/ር አዲል አብደላ
“ይሁንና ሁኔታዎች በዚሁ አይቀጥሉም፣ አንድ ቀን ይስተካከላል በሚል ተስፋ በምንችለው መጠን ተግተን መስራታችንን እንቀጥላለን፡፡ ፈተናዎቹን እየተጋፈጥን ላለመውደቅ መታገላችን የምርጫ ብቻ ሳይሆን የህልውናችንም ጉዳይ በመሆኑ የተለያዩ ስልቶችን እየቀየስን እንራመዳለን” ሲሉ ተናግረዋል፡፡
የስማርት ድርጅቶች የስራ ሃላፊዎች በየዘርፉ ካሉ ሰራተኞች ጋር ይበልጥ በመቀራረብ በስራ እንዲተጉና እንዲያተጉ የአደራ መልዕክታቸውን ያስተላለፉት ዶ/ር አዲል አብደላ በስራ ጉዳይ ለወራት በአገር ውስጥ ባልነበሩበት ጊዜ ፈታኝ ሁኔታዎችን በመቋቋም ሰራተኞች ላደረጉት ትግልና ለተገኙ ውጤቶች ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

04/02/2020
የአድራሻ ለውጥ - ከጄቪስ ሌዘርቀድሞ ከነበረበት ፒያሳ ኤሊያና ሞል ወደ አትላስ ሩሚ በርገር ፊትለፊት ግሬስ ፕላዛ መዛወሩን ለክቡራን ደንበኞቹ ይገልጻል፡፡ስልክ፡- 0966334512
03/02/2020

የአድራሻ ለውጥ - ከጄቪስ ሌዘር
ቀድሞ ከነበረበት ፒያሳ ኤሊያና ሞል ወደ አትላስ ሩሚ በርገር ፊትለፊት ግሬስ ፕላዛ መዛወሩን ለክቡራን ደንበኞቹ ይገልጻል፡፡
ስልክ፡- 0966334512

እንኳን አደረሳችሁ!!ኢ ኤች ኤም ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለገና በዓል አደረሳችሁ በማለት በዓሉ የሠላም፣ የፍቅርና የደስታ እንዲሆንላችሁ ይመኛል፡፡መልካም በዓል!!
06/01/2020

እንኳን አደረሳችሁ!!
ኢ ኤች ኤም ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለገና በዓል አደረሳችሁ በማለት በዓሉ የሠላም፣ የፍቅርና የደስታ እንዲሆንላችሁ ይመኛል፡፡
መልካም በዓል!!

የገና ስጦታ!የ2012 ዓ.ም የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ አዳዲስ ፋሽን የሴት ቦርሳዎች ለቀናት ብቻ በሚቆይ ልዩ የዋጋ ቅናሽ ቀርበዋል፡፡ ጄቪስ ሌዘር ከ“እንኳን አደረሳችሁ” መልዕክቱ ጋ...
30/12/2019

የገና ስጦታ!
የ2012 ዓ.ም የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ አዳዲስ ፋሽን የሴት ቦርሳዎች ለቀናት ብቻ በሚቆይ ልዩ የዋጋ ቅናሽ ቀርበዋል፡፡
ጄቪስ ሌዘር ከ“እንኳን አደረሳችሁ” መልዕክቱ ጋር “ኑ የዚህ ልዩ አጋጣሚ ተጠቃሚ ሁኑ” ይላችኋል!!
አድራሻ፡- ፒያሳ ኤሊያና ሞል (ግራውንድ ፍሎር)
ስልክ +251966334512

የገና ስጦታየገና በዓልን ምክንያት በማድረግ እስከ በዓሉ የሚቆይ ልዩ ቅናሽ ከጄቪስ ሌዘርአድራሻ፡- ፒያሳ ኤሊያና ሞል (ግራውንድ ፍሎር)ስልክ፡ 0966334512
24/12/2019

የገና ስጦታ
የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ እስከ በዓሉ የሚቆይ ልዩ ቅናሽ ከጄቪስ ሌዘር

አድራሻ፡- ፒያሳ ኤሊያና ሞል (ግራውንድ ፍሎር)
ስልክ፡ 0966334512

የስማርት ምርጦች!በማኑፋክቸሪንግ፣ በኮንስትራክሽን፣ በአግሮ ኢንደስትሪ፣ በሆስፒታሊቲ (ሆቴልና ፈጣን ምግብ አቅርቦት)፣ በትምህርት፣ በመዝናኛ፣ በአገልግሎት ሰጪነትና በሌሎች ዘርፎች የተሰማሩ...
04/12/2019

የስማርት ምርጦች!

በማኑፋክቸሪንግ፣ በኮንስትራክሽን፣ በአግሮ ኢንደስትሪ፣ በሆስፒታሊቲ (ሆቴልና ፈጣን ምግብ አቅርቦት)፣ በትምህርት፣ በመዝናኛ፣ በአገልግሎት ሰጪነትና በሌሎች ዘርፎች የተሰማሩ ከ13 በላይ እህትማማች ኩባንያዎችን አቅፎ በማስተዳደር ላይ የሚገኘው ስማርት ማኔጅመንት ሰርቪስስ፤ የየኩባንያዎቹን የተግባር ሂደትና የሰራተኞቹን የስራ ትጋት ለማጎልበት ከሚጠቀማቸው ውጤታማ የአመራር ስልቶች መካከል “የወሩ ምርጥ ሰራተኛ”ን መምረጥና መሸለም አንዱ ነው፡፡
ይህ ለአጠቃላይ የድርጅቱ ሰራተኞች የስራ ተነሳሽነትና ትጋት የጎላ ድርሻ ያለው የአመራር ስልት፤ በስማርት የአስተዳደርና ፋይናንስ ቢሮ ስር በተቋቋመ ኮሚቴ የሚመራ ሲሆን፣ የየኩባንያዎቹ የስራ ሀላፊዎች በወሩ ውስጥ የተሻለ ትጋትና አፈጻጸም ያሳዩ ሰራተኞችን በመምረጥ ለዚህ ኮሚቴ እያቀረቡ ኮሚቴውም ባስቀመጠው መስፈርት መሰረት የተሻለውን ምርጥ መርጦ “ለወሩ ምርጥ ሰራተኛ” እውቅና እና ማበረታቻ ይሰጣል፡፡
በየወሩ የሚመረጡ ሰራተኞች ከግርጌው “Employ of the month/የወሩ ምርጥ ሰራተኛ” የሚል ጽሁፍ ያለበት ፎቶ ግራፋቸው ታትሞ በስማርት ማኔጅመንት ዋና መ/ቤት ውስጥ ሁሉም ሰራተኞች ሊያዩት በሚችሉበት ምቹ ቦታ ላይ ወሩን ሙሉ ከፍ ብሎ በክብር የሚቀመጥ ከመሆኑም ባሻገር ለሚመረጡ የወሩ ምርጥ ሰራተኞችም ትጋታቸውን የሚገልጽ የእውቅና ሰርተፊኬትና የገንዘብ ሽልማት ይበረከታል፡፡
እስካሁን ባለው ሂደት፡- ታሪኩ ገለታ (ከኢትዮጲስ ኮሌጅ)፣ ሃና አስናቀ (ከኢትዮጲስ ኮሌጅ)፣ ያስሚን መሐመድ (ከስማርት ፋይናንስ ቢሮ)፣ ሞላ ባዬ (ከጄቪስ አልሙኒየም)፣ ሃይማኖት ኪሮስ (ከኢትዮጲስ ኮሌጅ) … የየወሩ ምርጦች ሆነው የእውቅና ሰርተፊኬትና የማበረታቻ ገንዘብ ተሸላሚዎች ሆነዋል፡፡
የወሩ ምርጥ ሰራተኛ ሽልማት በስማርት ማኔጅመንት ሰርቪስስ እና በስሩ ባሉ በርካታ የእህት ኩባንያ ሰራተኞች ዘንድ በየወሩ በጉጉት የሚጠበቅና “ቀጣዩ ምርጥ ማን ይሆን?...ማን ትሆን?” በሚል የሚያነጋግር ለመሆን በቅቷል፡፡

“ቀጣዩ የስማርት የወሩ ምርጥ ሰራተኛ ማን ይሆን?...ማን ትሆን?”

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethio-Transport and Logistics International Exhibition posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Ethio-Transport and Logistics International Exhibition:

Share