Ethiopian Shipping and Logistics

Ethiopian Shipping and Logistics Vision
By providing competitive shipping & logistics services, to become a preferred & renowned Afric
(1)

29/04/2026

#የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ የ2018/19 የምርት ዘመን ማዳበሪያ አቅርቦትን በተያዘው የበጀት ዓመት ዘጠኝ ወራት ብቻ 1 ሚሊየን 556 ሺህ 157 ቶን በማጓጓዝ ለግብርናው ዘርፍ ያለውን ቁርጠኝነት አረጋግጧል።
የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ በበጀት ዓመቱ የዘጠኝ ወራት አጠቃላይ የኦፕሬሽን አገልግሎቱን በማሳደግ የዕቅዱን 109 በመቶ ማሳካት የቻለ ሲሆን፣ ይህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ22 በመቶ ብልጫ ያለው ነው።
ይህ ስኬት በተለይ እንደ ማዳበሪያ ያሉ ስትራቴጂካዊ የሀገር ውስጥ ግብዓቶች ሳይስተጓጉሉ ወደ ተጠቃሚው እንዲደርሱ በማድረግ ረገድ ፋይዳው የጎላ ሲሆን ከአገልግሎት አሰጣጥ ፍጥነት አንጻርም በጂቡቲ ወደብ የኮንቴይነር ቆይታን ለማሳጠር በተደረገው ጥረት፣ የቆይታ ጊዜውን ከታቀደው 7 ቀን ወደ 4.89 ቀናት ዝቅ ማድረግ ተችሏል።
ይህም እንደ ማዳበሪያ ያሉ ወቅታዊ ግብዓቶች በፍጥነት ተጓጉዘው ለገበሬው እንዲደርሱ ምቹ ሁኔታን ከመፍጠሩ በተጨማሪ ድርጅቱ መንግስት የግብርና ምርታማነትን ለማሳደግ ያስቀመጠውን አቅጣጫ በመከተል፣ ለግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽን ከሚሰጠው የየብስ ትራንስፖርት አገልግሎት ጋር በተያያዘ ከ28.1 ቢሊየን ብር በላይ የሚገመት የትራንስፖርት አገልግሎት በማቅረብ ላይ ይገኛል።
የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ በቀጣይም ዘመናዊ፣ ቀልጣፋና ወጪ ቆጣቢ የሆነ የሎጅስቲክስ አገልግሎትን በማቅረብ የሀገሪቱን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ የሚደረገውን ጥረት በላቀ ደረጃ ለመደገፍ በትኩረት እየሰራ ይገኛል።

28/04/2026

እነሆ ከሳምንታዊ ዜና እና ፕሮግራማችን ጋር

Ethiopian Shipping & Logistics wishes a productive and successful week to all our valued customers, stakeholders, manage...
27/04/2026

Ethiopian Shipping & Logistics wishes a productive and successful week to all our valued customers, stakeholders, management, and dedicated staff.

Your continued trust and commitment drive us forward every day. Together, let’s make this week another milestone in delivering excellence, reliability, and seamless service.

🚢 Moving beyond limits. Connecting possibilities.

Beyond The Sea.

25/04/2026

the Sea!

Across the oceans,through modern ports, along every road…
Ethiopian Shipping and Logistics moves your cargo with strength, precision, and care.
From sea to inland-seamlessly connected, reliably delivered.
Beyond the Sea!
We connect your world.

የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አዳዲስ መዳረሻ ወደቦችን በመጨመር ለደንበኞቹ ተደራሽ አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ ያውቃሉ?የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ከዚህ ዓመ...
23/04/2026

የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አዳዲስ መዳረሻ ወደቦችን በመጨመር ለደንበኞቹ ተደራሽ አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ ያውቃሉ?
የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ከዚህ ዓመት ጀምሮ የአገልግሎት አድማሱን በማስፋት ወደ ሩቅ ምስራቅ ሀገራት ጃፓን፣ ደቡብ ኮሪያ እና ኢንዶኔዥያ ወደሚገኙ ወደቦች አዳዲስ የጉዞ መስመር በመክፈት ለደንበኞቹ አስተማማኝ፣ ቀልጣፋና ተደራሽ የሆነ የባሕር ትራንስፖርት አገልግሎት እየሰጠ ነው፡፡
ድርጅቱ የራሱን 10 መርከቦች በመጠቀም ከአሁን ቀደም በመደበኛነት ከሚሰማራባቸው ከቻይና፣ ህንድና ገልፍ አገራት ከሚገኙ መዳረሻ ወደቦች በተጨማሪ አዳዲስ የንግድ መዳረሻ ወደቦችን መጨመሩ ለደንበኞቹ ተደራሽ የሆነ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ነው፡፡
የድርጅቱ መርከቦች የተለያዩ የጭነት ዓይነቶችን የመጫን አቅም ያላቸው (Multi-Purpose) በመሆናቸው በዋናነት ለኮንስትራክሽን አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ማሽነሪዎች እና ሌሎች ገቢ ዕቃዎችን ለማጓጓዝ ምቹ፤ ለደንበኞች ተመራጭ እንዲሁም በጊዜ እና በወጪ ረገድም ተወዳዳሪ የለሾች ናቸው፡፡
የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ የገበያ ፍላጎትን እና የአዋጭነት ጥናትን መሠረት ያደረገ አዳዲስ መዳረሻ ወደቦችን በመክፈት አገልግሎቱን የማስፋት ዕቅድ እንዳለው ስናሳውቅዎ በታላቅ ደስታ ነው፡፡
የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ
Beyond The Sea!

20/04/2026

እነሆ ሳምንታዊ የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ፕሮግራማችን

In international trade, trust moves everything. Your cargo deserves to arrive safely, on time, and without compromise.Et...
18/04/2026

In international trade, trust moves everything. Your cargo deserves to arrive safely, on time, and without compromise.
Ethiopian Shipping and Logistics (ESL) delivers reliable, efficient, and fully accountable import and export solutions—moving your goods seamlessly from origin to destination.
From global export shipments to imports delivered to dry ports, industrial parks, free trade zones, and authorized customs warehouses, we handle every step with precision and care.
By sea or land, our team ensures your cargo arrives intact and on schedule—because delays cost more than time.
Partner with us for dependable logistics that power your business growth.
Move your cargo beyond borders with confidence.

📞 Contact us today with 0951414207

Shipping and Logistics (ESL)
The Sea!

የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ እና የኢንደስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በጋራ መስራ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ  ውይይት አደረጉ፡፡የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ እ...
16/04/2026

የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ እና የኢንደስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በጋራ መስራ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት አደረጉ፡፡
የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ እና የኢንደስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮችዛሬ በሞጆ ሎጀስቲክስ ማዕከል ተገኝተው ውይይት ባደረጉበት ወቅት ሁለቱም የመንግስት የልማት ድርጅቶች እንደመሆናቸው የሀገርን ኢኮኖሚ በሚያገዝፉ፣ ለዜጎች የስራ ዕድል በሚፈጥሩና የሎጀስቲክስ ዘርፉን ገቢ በሚያልቁ ጉዳዮች ላይ በአብሮነት መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ውጤታማ ውይይት አድርገዋል፡፡
በኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢንጂነር አብዱልበር ሸምሱ እና በኢንደስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍስሃ ይታገሱ (ደ/ር) የተመራው ይኸው የከፍተኛ አመራሮች ቡድን በሞጆ ሎጀስቲክስ ማዕከል ተገኝቶ የሎጀስቲክስ የመሰረተ ልማት ስራዎችንና የማስፋፊያ ግንባታውን ተዘዋውረው ከተመለከቱ በኋላ በሰጡት አስተያየት እንደ ዜጋ ክብር የተሰማቸው እና የሀገራችን ብልጽግና አይቀሬ ስለመሆኑ የተገነዘቡበት እንደሆነ አንስተዋል፡፡
ከጉብኝቱ በኋላ ከሁለቱም ድርጅቶች በአብሮነት ለመስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ የመነሻ የመወያያ ጽሑፍ የቀረበ ሲሆን በተለይ በኢንደስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በኩል በቀረበው መወያያ በድሬዳዋ ወደብና ድሬዳዋ ነፃ ንግድ ዞን መካከል ባለው 500 ሄክታር ቦታ ላይ በጋራ ማልማት ቢቻል ለ 100 ሺህ ዜጎች የስራ ዕድል መፍጠር የሚቻል ስለመሆኑ ተመላክቷል፡፡
በኢባትሎ በኩል በቀረበው የመወያያ ጽሑፍም በኢንደስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ውስጥ በተለያዩ ክልሎች የሚገኙ አምራች ድርጅቶች በአስመጪነትም ሆነ በላኪነት ከኢባትሎ ጋር ለሚሰሩ የተለያዩ ጥቅማጥቅሞች መዘጋጀታቸውን ገልፀው የአብሮነት ስራው የአምራቾቹን ስራ ውጤታማ የሚያደርግ ከመሆኑም ባሻገር አምራቾቹ ዘንድ ሀገር ልታገኝ የሚገባትን የሎጀስቲክስ ዘርፍ ጥቅም አሟጣ እንድትጠቀም ሊያደርግ እንደሚችል በማንሳት አይ ፒ ዲ ሲ ም የአብሮነት ስራው እንዲሳካ የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያበረክት ተጠይቋል፡፡
በሁለቱም የልማት ድርጅቶች በኩል የቀረበውን የመወያያ ጽሑፍ መነሻ በማድረግ በከፍተኛ አመራሩ ደረጃ የቀረቡትን ሃሳቦች ወደ ተግባር ለማሸጋገር እንዲቻል የጋራ ኮሚቴ ኮሚቴ እንዲቋቋም ስምምነት ላይ ተደርሶ ኮሚቴ እንዲቋቋም ተደርጓል፡፡ ኮሚቴው በየጊዜው የደረሰበትን ለከፍተኛ አመራሩ እያቀረበ እንዲያሰገመግም አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡

16/04/2026
13/04/2026

A New Week, A Renewed Journey ⚓️

As we step into a new week following the joy and reflection of Easter, Ethiopian Shipping and Logistics wishes you a fresh start filled with hope, strength, and success.

Just as our vessels move forward across the seas with purpose, may your week sail smoothly toward new opportunities and achievements.

We remain committed-reliable, resilient, and always moving forward to serve you better.

Happy New Week!
Ethiopian Shipping and Logistics
Beyond the Sea! 🌊

Address

Around Leghar
Addis Ababa

Opening Hours

Monday 08:00 - 17:00
Tuesday 08:00 - 17:00
Wednesday 08:00 - 17:00
Thursday 08:00 - 17:00
Friday 08:00 - 17:00
Saturday 08:00 - 12:00

Telephone

+251115518280

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian Shipping and Logistics posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Ethiopian Shipping and Logistics:

Share