Tegenie Gudisa Customs Clearing

Tegenie Gudisa Customs Clearing CUSTOMS CLEARING , Freight Forwarding, Shipping Egent

31/03/2022

#ቼክ ምንድን ነው❓

ቼክ ማለት ገንዘብን ተክቶ የሚያገለግል ተላላፊ የገንዘብ ሰነድ ነው፡፡ ቼክ ሊፈርም የሚችለው በአንድ ባንክ ውስጥ ተንቀሳቃሽ ሂሳብ ያለው ሰው ነው፡፡ድርጅት ከሆነ ደግሞ ፈራሚው በድርጅቱ ቼክ ላይ የመፈረም ስልጣን የተሰጠው መሆን አለበት፡፡

ቼክ ከመቀበላችሁ በፊት በቼኩ ላይ -የሚከፈለው የገንዘብ መጠን በአሀዝና በፊደል መፃፉን - የሚከፈለው ሰው ስም እና የባንኩ ቅርንጫፍ መፃፉን -ቼኩን የሰጠው ሰው ፊርማ መኖሩን -ቼኩ የተፃፈበት ቀን እና ቦታ መኖሩ ማረጋገጥ የግድ አስፈላጊ መሆኑን የንግድ ህግ አንቀፅ 827 ይደነግጋል።

ቼኩ ለማን እንደሚከፈል ስም ካልተጠቀሰበት ማንኛውም ቼኩን ይዞ የቀረበ ሰው ይከፈለዋል። ቼኩ በስሙ የተፃፈለት ሰው ወይም በትዕዛዝ የሚል ካለበት ደግሞ በቀላሉ ከጀርባው በመፈረም ለሌላ ሰው ሊያስተላልፈው ይችላል ።ያም ሰው በጀርባው ፈርሞ ለሌላ ሰው ማስተላለፍ ይችላል፡፡ -የገንዘብ መጠኑ ያልተጠቀሰበትን ቼክ ፈርሞ መስጠት አደገኛ ነው ፡፡ ቼኩ የተፃፈለት ወይም የተላለፈለት ሰው የፈለገውን ገንዘብ ሊሞላበት ይችላል፡፡

ቼኩ የሚከፈለው ለባንኩ ለክፍያ በቀረበ ቀን ነው። - ሆኖም ቼኩ በን/ሕ/ቁ 857 መሠረት የወጣበት ቀን ከግምት ሳይስገባ ቼኩ ላይ ከተፃፈው ቀን ጀምሮ በ6 ወር ውስጥ ለባንኩ ለክፍያ መቅረብ አለበት፡፡ -ቼኩን የሚፈርመው ሰው የክፍያውን ቀን ቼኩን ከፃፈበት ወይም ቼኩን ካወጣበት ቀን ወደፊት ወይም ወደ ኋላ ሊያደርገው ይችላል። ለምሳሌ ዛሬ ቼኩን ሲፅፍ የተፃፈበት ቀን ወደኃላ 7 ወር አድርጎ ቀኑን ቢፅፈው ለክፍያ መቅረብ ያለበት 6 ወር ጊዜ ስላለፈ ባንኩ መክፈልም ሆነ ያልከፈለበትን ምክንያት ለመግለፅ ሳይገደድ ቼኩ ለክፍያ መቅረብ ባለበት ጊዜ ባለመቅረቡ ብቻ ይመልሰዋል፡፡

ዛሬ የሚሰጥ ቼክ ወደፊት የዛሬ 4 ወር አድርጎ ቀኑ ከተፃፈበት ለክፍያ መቅረብ የሚችለው ከአራት ወራት በኃላ ካለው ቀን ጀምሮ ባለው 6 ወራት ውስጥ ነው፡፡ ስለዚህ ቼክ ተቀባዬች የሚሰጣቸውን ቼክ ገንዘቡን መቀበል ከሚችሉበት ቀን አንፃር በጥንቃቄ የተፃፈበት ቀን ማየት ያስፈልጋል ::

-ቼክ የሰጠው ሰው ቼኩ ለባንኩ ለክፍያ ከመቅረቡ በፊት ባንኩን እንዳትከፍል ብሎ መከልከል ይችላል። ባንኩም የክፍያ መከልከያ ትእዛዝ ከደረሰው መክፈል የለበትም።

ቼኩን ለባንክ አቅርበህ በቼኩ ላይ የተጠቀሰውን ያህል በቂ ገንዘብ ከሌለ በሂሳቡ ውስጥ ያለውን ያህል መቀበል ይቻላል። ለቀረው ገንዘብ ደግሞ ባንኩ ‘‘በቂ ስንቅ ለውም’’ የሚል የፅሁፍ ማስረጃ ቼኩን ይዞ ለቀረበው ሰው ይሰጠዋል። -በተለምዶ ‘‘ደረቅ ቼክ’’ የሚባለው ለክፍያ ሲቀርብ በሂሳቡ ውስጥ በቂ ገንዘብ ከሌለው ሲሆን ባንኩ በሚሰጠው ማስረጃ መሰረት ቼክ ሰጪውን ወይም አውጭውን በወንጀል ያስጠይቃል። ሆን ተብሎ ከተፈፀመ ቼክ አውጪው በወንጀል ህግ አቀፅ 693 መሰረት በቀላል እስራት ወይም ነገሩ ከባድ ከሆነ ደግሞ ከአስር አመት በማይበልጥ ፅኑ እስርና በመቀጮ ይቀጣል።

ደረቅ ቼኩ የተሰጠው በቸልተኝነት ከሆነ ደግሞ ሰጭው በመቀጮ ወይም ከአንድ አመት በማይበልጥ ቀላል እስር ይቀጣል ፡፡ -ሳይከፈል የቀረውን የቼኩን ገንዘብ ና ወጭውን ቼኩ የተፃፈለት ወይም ተፈርሞ የተላለፈለት ሰው በፍትሀ ብሔር ከሶ ገንዘቡን ማስመለስ ይችላል፡፡ -በብሔራዊ ባንክ መመሪያ መሰረት ደረቅ ቼክ የሚሰጡ ሰዎች በጥፋታቸው በጥቁር መዝገብ ውስጥ የሚገቡ ሲሆን ከገንዘብ መቀጮ አንስቶ በቼክ ሂሳብ የማንቀሳቀስ መብታቸውን እስከማሳጣት ቅጣት ይጣልባቸዋል፡፡

©https://t.me/ethiopreneure
እንዲሁም ከዚህ በፊት የለቀቅኳቸውን ቪዲዮዎችን ብትከታተሉ ምርጥ እውቀትን ልታገኙ ትችላላችሁ
አሁንም የቴሌግራምና የYouTube ቻናሌን Subscribe በማድረግ ድጋፋችሁን አሳዩኝ።
✅✅✅ #ያወቁትን ማሳወቅ ብልህነት ነው!✅✅✅

የ YouTube ቻናል ሊንክ 👇👇👇
https://www.youtube.com/channel/UCZBIP6PqUdmmagdTjbyp_AQ

ቴሌግራም ቻናል
👇👇👇👇👇👇 https://t.me/MuhammedComputerTechnology

29/03/2022
21/03/2022

ሀ) በማንኛዉም የጉምሩክ አገልግሎቶች ቅድሚያ የማግኘት፤
ለ) ከጉምሩክ አሰራር ጋር በተያያዘ ህጎች ሲወጡ ከመጽደቃቸዉ በፊት የመሳተፍ፤ ከፀደቁ በኋላ በቋሚነት እንዲደርሳቸዉ ማድረግ፤
ሐ) ለሚያቀርቡ ቅሬታዎች እና አቤቱታዎች ቅድሚያ የመገልገል መብት፤
መ) ማናቸዉም የጉምሩክ መረጃዎችን በፍጥነት የማግኘት መብት፤
የፕሮግራሙ ተጠቃሚ ድርጅት ግዴታ
በተመረጡ የኢኮኖሚ አንቀሳቃሾች ፕሮግራም የታቀፈ ድርጅት የሚከተሉትን ግዴታዎች ሊወጣ ይገባል፡፡
ሀ) የገቢም ሆነ ወጪ ዕቃዎች ለፍተሻ እና ሰነድ ምርመራ ሲመረጡ ተባባሪ መሆን፤
ለ) በፕሮግራሙ ተጠቃሚ በመሆኑ ምክኒያት በዚሁ አሰራርና በሌሎች ህጎች የተሰጠዉን መብት በአግባብ መጠቀም፤
ሐ) በድህረ ዕቃ አወጣጥ ኦዲት ሂደት ተባባሪ መሆንና አስፈላጊ ሰነዶችን ማቅረብ፤
መ) በጉምሩክ የሚፈለግባቸዉን ቀረጥና ታክስ በታማኝነት የመክፈል፤
ሠ) በሀገር ዉስጥ ገቢ የሚፈለግባቸዉን ክፍያ በወቅቱ እና በትክክል አሳዉቆ መክፈል፤
ረ) ከፕሮግራሙ ጋር ተያያዥነት ያላቸዉ መረጃዎች ሲጠየቅ ለኮሚሽኑ በመስጠት ተባባሪ መሆን፤
ሰ) ከሎጂስቲክሱ ጋር የተያያዘ የዉስጥ የአሰራርና የሲስተም ለዉጥ ሲያደርግ በወቅቱ ለኮሚሽኑ ማሳወቅ፤
ሽ) አዳዲስ ማስፋፊያዎች ሲያደርግ ወይም በተለያየ ምክኒያት ቢዘጋ ለኮሚሽኑ ማሳወቅ፤
ቀ) የፕሮግራሙ ተጠቃሚ ለመሆን በተፈራረመዉ የስምምነት ሰነድ መሰረት የፕሮግራሙ ተጠቃሚነት ሰርተፍኬት የአገልግሎት ጊዜዉ ከመጠናቀቁ በፊት የእድሳት ጥያቄ ለኮሚሽኑ ማቅረብ፤
በ) የስራ እና የቦታ ለዉጥ ሲያደርግ በወቅቱ ለኮሚሽኑ ማሳወቅ፤
ተ) የስነ ምግባር ችግር ያለባቸዉ ሰራተኞች እየለየ እንደ ጥፋቱ መጠን እርምጃ መዉስድ እና ለኮሚሽኑ የማሳወቅ፤
ቸ) ከሎጂስቲክስ ጋር በተያያዘ የሚገጥመዉን ችግር በየወቅቱ ሪፖርት ማድረግ እና ችግሮችን በጋራ ለመፍታት ዝግጁ መሆን ይጠበቅበታል፡፡

ክፍል አስራ አንድ ይቀጥላል…
ለተጨማሪ መረጃ፡-
E በፌስቡክ:- https://fb.com/modjcustoms
E በቴሌግራም ፡- https://t.me/joinchat/VwFmMACRcvG0H2f7
E በኢሜይል ፡- [email protected]
E በስልክ ቁጥር ፡- 0221161745/0222364434

20/03/2022

የእንቅልፍ አተኛኘት አቅጣጫ ጥሩ እና መጥፎ ጎናቸው!
1. በጀርባቸው የሚተኙ!
🔻 ጥቅሙ
በጀርባ መተኛት ትራስ አከርካሪን የመደገፍ ሥራውን በትክክል እንዲወጣ ይረዳዋል። በትክክለኛው አለም ሁሉም ሰው ትራስ ሳይጠቀም በጀርባው መተኛት ይፈልጋሉ፤ ይህም አቅጣጫ አንገታችን ነፃ አቅጣጫ ላይ እንዲሆን ይረዳዋል። ከመጠን በላይ/ብዙ ትራስ መጠቀም የአተነፋፈስ ሥርዓትን አስቸጋሪ ያደርገዋል።
በጀርባ መተኛት ውበትን ከመጠበቅ አንፃር ይመከራል፤ ሌሊቱን ሙሉ ፊታችን ለንጽህ አየር እንዲጋለጥ በማድረግ ይረዳል። የተጠቀምነው የውበት መጠበቂያ ኮስሞቲክስ በትራሱ እንዳይጠረግ ከማድረጉ በተጨማሪ የፊት መሸብሸብን ወይም መጨማደድን ይቀንሳል።
🔻 ጉዳቱ
ማንኮራፋት እና የእንቅልፍ እጦት በጀርባ ተንጋሎ ከመተኛት አቅጣጫ ጋር ይያያዛሉ። በነገራችን ላይ በጀርባ መተኛት ከእንቅልፍ እጦት ጋር በቅርበት የተገናኘ ነው ለዚህም ነው ዶክተሮች በጎን አቅጣጫ በኩል መተኛትን እንደመፍትሄ የሚመክሩት።
በጀርባችን በምንተኛበት ወቅት የመሬት ስበት ሃይል የምላሳችን ሥር ወደ አየር ቧንቧ አቅጣጫ እንዲታጠፍ ያስገድደዋል ይህም ሥርዓተ ትንፈሳን በማስተጓጎል ጎረቤትን እንቅልፍ የሚነሳ አስቀያሚ ማንኮራፋት እንዲፈጠር ያደርጋል።
ጥሩ እንቅልፍ የሚተኙ እና ጥሩ ያልሆነ እንቅልፍ የሚተኙ ሰዎችን በማነፃፀር የተደረገ ጥናት እንደሚያሳየው፦ ጥሩ ያልሆነ እንቅልፍ የሚተኙ ሰዎች አብዛኛውን የመኝታ ጊዜ የሚያሳልፉት በጀርባቸው እንደሆነ አረጋግጠዋል።
2. በጎናቸው የሚተኙ!
🔸 ጥቅሙ
በጎናቸው የሚተኙ ሰዎች በአንድ ላይ! ማህፀን ውስጥ እንዳለ ጽንስ እግራቸውን እጥፍጥፍ አድርገው የሚተኙ እና እግራቸውን ዘርግተው የሚተኙ ሰዎች፤ አብዛኛው ማህበረሰብ በጎን በኩል እንደሚተኙ ሪፓርት ተደርጓል።
በእርግዝና ወቅት በግራ ጎን በኩል እንዲተኙ ዶክተሮች ይመክራሉ፤ ምክንያቱም ወደ ልብ ያለውን የደም ፍሰት ስለሚጨምር ነው ይህም ለእናት እና ልጅ እጅግ በጣም ጠቃሚ ነው።
በእርግዝና ወቅት በጎን በኩል እንድትተኚ ይመከራል ምክንያቱም በጀርባ በኩል መተኛት የታችኛው ጀርባ ላይ ግፊት ይፈጥራል (በአብዛኛው ፌንት እንድታደርጊ አስተዋጽዎ ያድርጋል)። እንደሚታወቀው በእርግዝና ወቅት በሆድ በኩል መተኛት አይቻልም።
🔸 ጉዳቱ
በተመሳሳይ ሁኔታ በግራ ጎን በኩል መተኛት ሆድ እና ሳንባ ላይ ጫና እንዲፈጠር ያደርጋል። ሁሉም በጎናቸው የሚተኙ ሰዎች እንደሚያውቁት በዚህ አቅጣጫ በሚተኙበት ወቅት የእጅ መደንዘዝ ሊያጋጥም ይችላል።
ጭንቅላትን እጅ ላይ አስደግፎ መተኛት የተለመደ አቅጣጫ ነው። ነገር ግን በጡንቻ እና ነርቭ ላይ ተጨማሪ ጉዳት ያስከትላል። ጭንቅላትን (አጠቃላይ ሰውነትን) በአንድ እጅ ላይ ማሳረፍ የደም ፍሰትን ይከለክላል በተጨማሪም ነርቭን ወደታች ይጫናል።
3. በሆዳቸው የሚተኙ!
🔹 ጥቅሙ
በሆድ በኩል መተኛት ማንኮራፋት እና የእንቅልፍ ችግርን ያስቀራል። ነገር ግን በጣም ጥሩ የሚባለው ጎኑ በሌሊት ሠዓት ቦርጫችን ወደ ውስጥ እንዲገባ ያደርጋል።
🔹 ጉዳቱ
በሆድ በኩል መተኛት በአብዛኛው እንደሚታወቀው በጣም አስቀያሚ የሚባል የአተኛኘት አቅጣጫ ነው።
የአከርካሪ የተፈጥሮ መንጋደድን በማዛባት ቀጥ እንዲል ያደርገዋል ይህም የታችኛው ጀርባ ህመምን ያስከትላል።
ሌሊቱን ሙሉ ጭንቅላትን ወደ አንድ አቅጣጫ አድርጎ መተኛት የአንገት ህመምን ያስከትላል። ይህ የአተኛኘት አቅጣጫ ምርጫዎ ከሆነ ትራስ በመጠቀም ሰውነትዎ በአንድ አቅጣጫ መተኛትም ያለማምዱት።
▬▬ Share ▬▬▬▬
ለተጨማሪ እውቀት እና ጠቃሚ የቴክኖሎጂ መረጃ ለማግኘት በዚ የቴሌግራም ቻናላችንን ከታች ባለዉን ሊንክ በመጫን ማግኘት ይችላሉ።
here it is
https://t.me/Information_Science_Technology
በተጨማሪም ዩቲዩብ ቻናላችንን በመቀላቀል በምስል እና በቭድዮ የተዘጋጁ ከስራ እና ከቴክኖሎጂ ጋር ይተዋወቁ Subscribe በማድርግ ሌሎች መረጃዎች ይሸምቱ
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/channel/UCpKx7Pd_viT9nnmheRu6o8Q

20/03/2022

🛑⁉️ፋይል ከኮምፒውተር፣ ከፍላሽ ዲስክ፣ ከExternal ሀርድ ዲስክ፣ ከCD፣ ሳታስቡትና አስባችሁት ፎርማት ወይም ድሌት ቢሆንባችሁ እንደግና መመለስ ፈልጋችሁ ነገር ግን መልስ አጥታችሁ ይሆናል ስለዚህ በመጀመሪያ ደረጃ ሪከቨሪ ሶፍትዌሩን ከቴሌግራም ቻናሌ ገብታችሁ ዳውንሎድ በማድረግ ኮምፕዩተራችሁ ላይ መጫን ይጠበቅባችኋል ከዛም ከዚህ በታች ያለውን ቅደም ተከተል ተከተሉ።
በመጀመሪያ ደረጃ የተጫነውን ሪከቨሪ ሶፍትዌር ስትከፍቱት ከዚህ በታች እንደጻፍኩት ይመጣላችኋል።
✒️ Welcome to the Recuva Wizard
File Type what sort of file you trying to recover?
⏺ All files
⏺ Pictures
⏺ Music
⏺ Documents
⏺ Video
⏺ Compress
⏺ Emails
📍 7 አማራጭ ያመጣልናል። እናንተ መመለስ የምትፈልጉት ከላይ ከተጠቀሱት ሁሉንም ከሆነ ✅ All Files የሚለውን ይጫኑ። ከዛውጭ ግን ለምሳሌ Video ከሆነ ✅ Video የሚለውን ይጫኑ።
📍 File location Where were the file?
⏺ In A specific Location Browse... የሚለውን በመጫን ሲመጣልን Local Diak (C:) ሌላም ይመጣል የምንፈልገውን drive እንምረጥለት ለምሳሌ የፍላሽ ዲስክ ከሆነ እንመረጣለን ከዛም Ok እንጫናለን።
✅ Next እንጫናለን
✅ Enable Deep Scan click በማድረግ
✅ Start እንጫናለን
✅ ስካን በማድረግ ይ ፕሮግረስ 100% እስከሚል ድረስ መጠበቅ የተሻለ ነው ግን በመጫን አቋርጠን የሚመጣልን recover የተደረገውን ያመጣልናል ከዛም በግራ በኩል መጀመሪያ ላይ Filename ✅ የራይት ምልክት ያድረጉ። ከዛውጭ የምትፈልጉትን የራይት ምልክት በማድረግ ከታች ... የሚለውን በመጫን
✅ ሪከቨር የተደረገውን ፋይል የምታስቀምጡበትን ቦታ ይምረጡና የሚለውን ይጫኑ። አለቀ! እንኳን ደስ አላችሁ ፋይላችሁን መለሳችሁት!
ይህ መረጃ ብዙ ሰዎችን ስለሚጠቅማቸው ሼር ያድርጉ!
ከተማቻችሁ አስተያየት ይስጡኝ!
◄◄ሼር▻▻
በምስል እና በቪድዮ የተደገፍ አስተማሪ ይዘት ያላቸው ቁምነገሮች እየሰራን ስለሆነ ከዚህ በታች ባለው YouTube channel ሊንክ በመግባት Subscribe በማድረግ ያበረታቱን ዘንድ በትህትና እንጠይቃለን::
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/channel/UCpKx7Pd_viT9nnmheRu6o8Q

19/03/2022

👉 ውድ ደንበኞቻችን ማንኛውም የቀረጥ ተመላሽ ጥያቄ ወደ ቀረጥ ተመላሽ ስራ ክፍል ሲያቀርቡ ከታች በማስታወቂያው የተዘረዘሩትን ቅደመ-ሁኔታዎች ማሟላትዎን አይዘንጉ፡፡

17/03/2022

ያለካርድ ከኤቲኤም ገንዘብ ማውጣት ይቻላል!
========
በሲቢኢ ብር አገልግሎት አማካኝነት በኤቲኤም ማሽን ብር ወጪ እንዲሆን በማዘዝ እና በኤቲኤም ማሽኑ የሚጠየቁትን ብር የተላከበትን የስልክ ቁጥር፥ የሚስጥር ቁጥር እንዲሁም የተላከውን የገንዘብ መጠን በማስገባት ያለካርድ ገንዘብ ማውጣት ይችላሉ፡፡

አገልግሎቱን ለማግኘት የአጠቃቀሙን መመሪያ በሚከተለው ማስፈንጠሪያ ማግኘት ይችላሉ፡
https://www.facebook.com/photo?fbid=304719065020680&set=a.291948902964363 ወይም https://www.youtube.com/watch?v=nRXLtx36xAc

16/03/2022

ስለ ታሪፍ በጥቂቱ
1. ኖሜንክሌቸር፡- ማለት ሁሉንም በአለም የንግድ እንቅስቃሴ ውስጥ የሚዘዋወሩትን እቃዎችን ሲስተማቲክ በሆነ መልኩና በዓለም አቀፍ ህግ እና አተረጓጎም መሰረት አለም አቀፍ ኮድ ወይም ስም እንዲይዙ የማድረግ ዘዴ ነው፡፡
2. የጉምሩክ ታሪፍ፡- የአገሮችን ጥቅም እና የጉምሩክ ምጣኔ ሬት መሰረት በማድረግ የአለም የጉምሩክ ድርጅት ካወጣው የዕቃዎች ኮድ በማይጣረስ መልኩ በአለም የንግድ እንቅስቃሴ ውስጥ የሚዘዋወሩትን እቃዎችን ሲስተማቲክ በሆነ መልኩና በዓለም አቀፍ ህግ እና አተረጓጎም መሰረት ኮድ ወይም ስም እንዲይዙ የማድረግ ዘዴ ሲሆን በኢትዮጲያ ደረጃ በስምንት ዲጂት ይገለጻል፡፡
3. ክላሲፊኬሽን ፡-የአንድን ዕቃ የሚመደብበትን ኮድ የመጨረሻ አንቀጽ ወይም ንዑስ አንቀጽ የማግኘት ሂደት ነው፡፡
4. ብሔራዊ መግለጫ፡- በብሔራዊ ደረጃ የተከፋፈሉ የታሪፍ ቁጥሮች ብቻ የሚያብራሩ መግለጫዎች ናቸው፡፡
በአለም ዓቀፍ የሸቀጦች አሰያየምና አመዳደብ ሥርዓት ማለት በዓለም ዓቀፍ ንግድ ውስጥ የሚዘዋወሩ ሸቀጦች ወጥ በሆነ መልኩ የተሰጣቸው መለያ ኮድ ቋት እንዲኖራቸው በማድረግ በንግድ እንቅስቃሴ ውስጥ ፡-
1. የጉምሩክ ቀረጥ ለማስከፈል
2. ፈጣን የመረጃ ልውውጥ
3. በመረጃ ቴክኖሎጂ የተደገፈ የቁጥጥር ስርዓት
4 . መረጃ ላይ የተመሰረተ የንግድ ድርድር እና ስምምነት
5 . በመረጃ ላይ የተመሰረተ ኢንቨስትመንት
6 . ግልጽ እና ፈጣን የግብር አሰባሰብ
7. ጠቃሚ የሆኑ የማክሮ ኢኮኖሚ ውሳኔዎች እና የመሳሰሉት እንዲሰፍኑ በማድረግ ዓለም አቀፍ የሸቀጦች (እቃ) ንግድን የሚያሳልጥ የአሰራር ስርዓት ነው፡፡
እቃ ማለት ምን ማለት ነው?
እቃ ማለት ማንኛውንም ተንቀሳቃሽ ንብረት ሲሆን ግዙፍነት የሌላቸው በህግ እንደተንቀሳቃሽ ንብረት የሚታወቁትን ንብረቶችና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸውን በአገልግሎት ላይ የዋሉ የተፈጥሮ ሀይል ውጤቶችን እና የከርሰ ምድር ሀብትን የሚያካትት ሲሆን ገንዘብንም ይጨምራል፡፡
የኤች ኤስ ስምምነት (HS CONVENTION)
ስምምነቱ 20 አንቀጾች አሉት
ስድስቱን የሀርሞናይዝድ ሲስተም እ.ኤ.አ ከጃንዋሪ1/1998 ዓ.ም ጀምሮ በተግባር ላይ ከዋለበት ጊዜ ጀምሮ የሐርሞናይዝድ ሲስተም ኮንቬንሽን ፈራሚ የሆኑ አባል አገሮች ቁጥር በአሁኑ ጊዜ 160 Contracting Parties (159 countries and the European Union) ደርሷል፡፡ source: http://www.wcoomd.org/-/media/wco/public/global/pdf/topics/nomenclature/overview/hs-contracting-parties/list-of-countries/countries_applying_hs.pdf?db=web october 1/2020 በሲስተሙ የሚጠቀሙ ሃገራት ደግሞ 170 ሲሆኑ የኢኮኖሚ ህብረቶችን ሲጨመሩ ቁጥሩ ከ200 በላይ ይሆናል፡፡ ሲስተሙን በዋናነት የሚጠቀሙበት በጉምሩክ ቀረጥ አሰራር እና ቁጥጥር ለሚደረግባቸው እቃዎች ሲሆን ኢትዮጲያ የሐርሞናይዝድ ሲስተም ኮንቬንሽን ፈራሚ አባል ስትሆን ሲስተሙ ለጉምሩክ ቀረጥ አሰባሰብና የወጪ እና ገቢ ዕቃዎችን የስታስቲክስ መረጃ ለማደራጀት እንዲያገለግል ከነሐሴ 1985 ዓ.ም ጀምሮ ተግባር ላይ አውላዋለች፡፡
የሀርሞናይዝድ ሲስተም ኖሜንክሌቸር የታሪፍ መጽሀፍ በየአምስት አመቱ ወቅታዊ ማሻሻያ የሚደረግበት ሲሆን በማሻሻያዎቹ መሰረት በዓለም ዓቀፍ ንግድ ውስጥ እንቅስቃሴዎች በጣም የቀነሰ ወይም የጠፉ እቃዎች ይዘውት የነበረውን የኤች ኤስ ኮድ እንዲለቁ ሲደረግ በዓለም አቀፍ ንግድ ውስጥ ዝውውራቸው እያደገ የመጡትን የአዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ውጤት የሆኑ ሸቀጦች ደግሞ የየራሳቸው ኤች ኤስ ኮድ እንዲይዙ ይደረጋል፡፡
በጉምሩክ አዋጅ 859/2006 አንቀጽ 102 መሰረት
ወደ ጉምሩክ ክልል የሚገቡ ማናቸውም ዕቃዎች ላይ የሚከፈል ቀረጥ በጉምሩክ የታሪፍ ደንብ በተወሰነው ምጣኔ መሰረት ይሆናል ጭነቱ በተለያየ የታሪፍ አመዳደብ የሚመደቡ እቃዎችን የያዘ በመሆኑ ምክንያት ዕቃዎችን የመመደብ ወይም ዲክላራሲዮን ማዘጋጀት ስራው አድካሚ ሆኖ ሲገኝና የጉምሩክ የታሪፍ ምጣኔ ልክ የተለያየ በሚሆንበት ጊዜ በዲክላራሲዮን አቅራቢው ጥያቄ መሰረት ሚኒስትሩ አጠቃላይ ጭነቱን ከፍተኛ ታሪፍ በሚመደብበት የታሪፍ መደብ ላይ በመመደብ የታሪፍ ምጣኔ ልኩ እንዲወሰን ሊፈቅድ ይችላል፡፡ የአለም የጉምሩክ ድርጅቶች ስለሸቀጦች አመዳደብ የሚያወጣው ሰነድ ስለ ዕቃዎች አመዳደብ ወሳኝ ማስረጃ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡
የኤች አስ ኮድ ጠቀሜታዎች
1. For negotiation - bilateral or multi lateral
2. It is common language for international trade
3. It is used for identify customs tariff and trade statistics
4. It used for custom control and procedure
5. It used for identify rules of origin quota control and trade monitoring

Address

Welo Sefer
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Tegenie Gudisa Customs Clearing posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Tegenie Gudisa Customs Clearing:

Share