Sol Entertainment / ሶል ኢንተርተይንመንት

31/08/2026
28/08/2026
09/08/2026

Enjoy the videos and music you love, upload original content, and share it all with friends, family, and the world on YouTube.

ወጋገን ባንክ እ.ኤ.አ በ2025/26 በጀት ዓመት ከታክስ በፊት የ4 ቢሊዮን ብር ትርፍ አስመዘገበጅማ፣ሐምሌ 11 ቀን 2018 ዓ.ምባንኩ ይህን ያስታወቀው የዳይሬክተሮች ቦርድ እና የስራ አመ...
19/07/2026

ወጋገን ባንክ እ.ኤ.አ በ2025/26 በጀት ዓመት ከታክስ በፊት የ4 ቢሊዮን ብር ትርፍ አስመዘገበ

ጅማ፣ሐምሌ 11 ቀን 2018 ዓ.ም

ባንኩ ይህን ያስታወቀው የዳይሬክተሮች ቦርድ እና የስራ አመራር አባላት በዛሬው ዕለት በጅማ ከተማ በኃይሌ ሪዞርት እያካሄዱ ባለው እ.ኤ.አ የ2025/26 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ ላይ ነው፡፡

በግምገማው ላይ በቀረበው የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት መሰረት ወጋገን ባንክ በተጠናቀቀው እ.ኤ.አ 2025/26 በጀት ዓመት የ16.2 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ ገቢ ያገኘ ሲሆን ይህም ከ2024/25 በጀት ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ21 በመቶ ብልጫ አለው፡፡ በተያያዘም ባንኩ በበጀት ዓመቱ ከታክስ በፊት የብር 4 ቢሊዮን ትርፍ አግኝቷል፡፡ በተመሳሳይም የባንኩ የተከፈለ ካፒታል ከባለፈው በጀት ዓመት አንፃር የ44 በመቶ ዕድገት በማሳየት ወደ ብር 10.1 ቢሊዮን እንዲሁም ጠቅላላ ሀብቱ ብር 110.7 ቢሊዮን ደርሷል፡፡

በተጨማሪም ባንኩ የሰበሰበው ተቀማጭ ገንዘብ ከ2024/25 በጀት ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ23 በመቶ ዕድገት በማሳየት ወደ ብር 81.6 ቢሊዮን ያደገ ሲሆን ፣ለተለያዩ የኢኮኖሚ ዘርፎች የሰጠው ብድርም ብር 67.3 ቢሊዮን ደርሷል፡፡ ባንኩ በበጀት ዓመቱ የሰበሰበው የውጭ ምንዛሬ ከባለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ34 በመቶ ብልጫ አሳይቷል፡፡

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Sol Entertainment / ሶል ኢንተርተይንመንት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share