29/08/2021
ተወገድ ከፊቴ ተፈታታኝ ሁሉ
ይረዳኛል ይረዳኛል ጊዮርጊስ ኃያሉ
የልዳው ሰማዕት ቅዱስ ጊዮርጊስ
ለፈለጉት ለወደደዱት ፈጥሮ ነው የሚደርስ
ነፍሴ አትጨነቂ ጽኚ በእምነት
አይተውሽም ፍጡነ ረድኤት
ሊወጠኝ ያገሳል የዚህ ዓለም አውሬ
ድረስልኝ ቅዱስ ጊዮርጊሰ ቋሚ ምስክሬ
በመተከዜን ልተው ልጽናና በመንፈስ
ይረዳኛል ይረዳኛል ሰማዕቱ ጊዮርጊስ