Ethio Djibouti Railway

Ethio Djibouti Railway EDR

ከኮንቴነር ባሻገር፤ኢትዮ- ጅቡቲ ባቡር በሎጂስቲክስ ዘርፉ በመደበኛነት ጥቅም ላይ የሚውሉ የኮንቴነር አይነቶችን ማለትም ባለ 20 እና 40 ጫማ ኮንቴነሮችን  (20 ft and 40 ft con...
23/05/2026

ከኮንቴነር ባሻገር፤

ኢትዮ- ጅቡቲ ባቡር በሎጂስቲክስ ዘርፉ በመደበኛነት ጥቅም ላይ የሚውሉ የኮንቴነር አይነቶችን ማለትም ባለ 20 እና 40 ጫማ ኮንቴነሮችን (20 ft and 40 ft containers) በመጠቀም የገቢና ወጪ ጭነቶችን በማጓጓዝ ጉልህ ድርሻ እያበረከተ ይገኛል።

በኮንቴነር የሚጓጓዙ ጭነቶችን ምቹና ቀልጣፋ ለማድረግ በዲጂታል አማራጭ የታገዘ አገልግሎት በመስጠት እና የኮንቴነር ማራገፊያ ደረቅ ወደቦችን በማደራጀት ወደ ግዙፍ የሎጂስቲክስ ማዕከልነት ተሸጋግሯል።

የሀገራችን ወጪና ገቢ ቁሳቁሶች በመጠንና በዓይነት ዕድገት ማስመዝገባቸውን ተከትሎ በኮንቴነር ብቻ ተገድቦ የቆየውን አገልግሎት ማስፋት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ የተለያዩ ጭነቶችን በማጓጓዝ አዲስ ምዕራፍ ከፍቷል። ይህ የሎጂስቲክስ ስትራቴጂካዊ ለውጥ የጭነት አቅማችንን በእጅጉ አሳድጎታል።

በዚህም የቁም እንስሳት ፣ ግዙፍ ማሽነሪዎች፣ በኤሌክትሪክ ኃይል የሚሰሩ የጭነትና አነስተኛ የቤት አውቶሞቢሎች፣ የኤሌክትሪክ አውቶብሶች፣ የዓለምአቀፉ ደረጃዎች ድርጅት (ISO) መስፈርቶችን ያሟሉ የዘይት ኮንቴይነሮችን በማጓጓዝ የሎጂስቲክስ ዘርፉ ላይ ተጨባጭ ለውጦችን ማስመዝገብ ችለናል።

እነዚህ ጭነቶች በሀገራችን እየተከናወኑ ለሚገኙ የልማት ስራዎች ሁነኛ ግብአት በመሆናቸው በፍጥነት ከወደብ በማንሳትና ወደ መዳረሻቸው በመውሰድ የሚጠበቅባቸውን አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረግ ተችሏል።

ግመሎችን ጨምሮ የቀንድ ከብቶችን በባቡር የማጓጓዝ ስራ መጀመሩ ሀገራችን ከዘርፉ ማግኘት የሚገባትን ጥቅም በተሻለ መንገድ እንድታገኝ አስችሏል።

በኤሌክትሪክ ኃይል የሚሰራው የባቡር መስመሩ 'አረንጓዴው ባቡር ለአረንጓዴ ትራንስፖርት' በሚል መሪ ሃሳብ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን በማጓጓዝ ሀገራችን ለተያያዘችው የማይበገር የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታ ዕውን መሆን የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ ነው።

ከኮንቴነር ጭነት ባሻገር የባቡር ጭነት ዓይነቶችን በመጠንና በዓይነት በማስፋት ፈጣን፣ አስተማማኝ እና ወጪ ቆጣቢ የሎጂስቲክስ አገልግሎትን የማላቅ ተግባራችን ይበልጥ ተጠናክሮ ይቀጥላል።

ከፍተኛ ክብደት ያላቸው ብረታ ብረቶች፣ ጣውላ እና መሠል  ቁሳቁሶችን ለማጓጓዝ የሚያስችል ሴንትራል ቢም ዋገን (Central Beam Wagons) - የባቡር ፉርጎ ወደ ስራ አስገብተናል። ለበ...
21/05/2026

ከፍተኛ ክብደት ያላቸው ብረታ ብረቶች፣ ጣውላ እና መሠል ቁሳቁሶችን ለማጓጓዝ የሚያስችል ሴንትራል ቢም ዋገን (Central Beam Wagons) - የባቡር ፉርጎ ወደ ስራ አስገብተናል።

ለበርካታ ዓመታት ያለሥራ ቆመው የነበሩት የባቡር ፉርጎዎቹ አስፈላጊ የቴክኒክ ፍተሻ ተደርጎላቸው ብቁ መሆናቸው በመረጋገጡ ወደ ስራ እንዲገቡ ተደርጓል።

ይህም ኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር በሎጂስቲክስ ዘርፉ እያበረከተ በሚገኘው ሀገራዊ የባቡር ጭነት አገልግሎት ላይ ተደማሪ አቅም እንዲኖረው አድርጓል።

እያንዳንዳቸው ሰባ (70) ቶን የመጫን አቅም ያላቸው ሃያ (20) ሴንትራል ቢም ዋገኖቹ ላለፉት ዓመታት በተለያዩ ባቡር ጣቢያዎች ያለስራ ቆመው የነበሩ ናቸው፡፡

አሁን ወደ አገልግሎት በመግባታቸው ብረቶችን ጨምሮ ረዣዥም ጣውላዎችና መሠል ቁሳቁሶችን በፍጥነት፣ በተወዳዳሪ ዋጋና በከፍተኛ መጠን በማጓጓዝ ለኢኮኖሚያዊ እድገት መፋጠን አይነተኛ ሚና መጫወት ጀምረዋል።

በተመሳሳይ ከዚህ ቀደም ከነዳጅ እጥረት ጋር በተያያዘ የተፈጠረውን ከፍተኛ የወጪና ገቢ ዕቃዎቸ ጭነት በባቡር የማጓጓዝ አማራጭን ይበልጥ ለማሳደግ የሚያግዙ ጎንዶላ ዋገኖችን (Gondola Wagons (CW 3 እና CW 4)) ወደ ሥራ ማስገባታችን ይታወሳል።

ጎንዶላ ዋገኖቹ የመንግሥት ሸቀጦች የጉምሩክ ቁጥጥርን በመዳረሻ ጣቢያ እንዲያገኙ በማድረግ የተሳለጠ የባቡር ምልልስ እንዲኖር ማድረግ ተችሏል።




Find us on: 👇👇👇

📌Facebook: https://www.facebook.com/share/15vDenutJd/?mibextid=wwXIfr

📌 Linkedin: https://www.linkedin.com/company/ethio-djibouti-railway-share-company/

📌 Telegram: https://t.me/ethiodjiboutirailway t.me+1t.me+1

📌Web: https://www.edrsc.com

📌TikTok:

📌youtube:https://www.youtube.com/channel/UCJCVzH-JGvnOPfsbrDFDIjQ

📌Call center: 9546

Message from Ethio-Djibouti Railway (EDR) CEO, Takele UmaEndless momentum ahead.We’ve reviewed our performance matrix ac...
16/05/2026

Message from Ethio-Djibouti Railway (EDR) CEO, Takele Uma

Endless momentum ahead.

We’ve reviewed our performance matrix across core operations and infrastructure development — and while we’ve stayed focused on our planned objectives, we know we still have a long way to go. But that only drives us further.

Every operational win and infrastructure milestone has been built on one unwavering goal: keeping cargo and trade moving along the Ethio-Djibouti Railway corridor.

14/05/2026



A discussion forum is being held at Ethio-Djibouti Railway S.C.

Freight forwarders, customs clearance agents, and shipping agents who came from Ethiopia and Djibouti to discuss operational performance, logistics challenges, and ways to strengthen cooperation for efficient railway cargo services.




Find us on: 👇👇👇

📌Facebook: https://www.facebook.com/share/15vDenutJd/?mibextid=wwXIfr

📌 Linkedin: https://www.linkedin.com/company/ethio-djibouti-railway-share-company/

📌 Telegram: https://t.me/ethiodjiboutirailway t.me+1t.me+1

📌Web: https://www.edrsc.com

📌TikTok:

📌youtube:https://www.youtube.com/channel/UCJCVzH-JGvnOPfsbrDFDIjQ

📌Call center: 9546

At Ethio Djibouti Railway (EDR), we have a dedicated team of highly qualified and fully licensed customs clearance profe...
04/05/2026

At Ethio Djibouti Railway (EDR), we have a dedicated team of highly qualified and fully licensed customs clearance professionals ready to provide you with a complete range of services.
We are always ready to help your business move forward with confidence!


21/04/2026


ኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር ለመጀመሪያ ጊዜ በሀገር ልጆች የገነባውን የ የባቡር መስመር ፕሮጀክትን በተመለከተ ቀጣዩን ዘገባ አቅርቧል።

Address

Furi
Addis Ababa
1000

Telephone

+251944021378

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethio Djibouti Railway posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Ethio Djibouti Railway:

Share