Sirius Transit and Logistics Service

Sirius Transit and Logistics Service Customs Transits and logistics service in Ethiopia

10/12/2025

ደብዳቤ ቁ፡ 01-1-34/1432
ሕዳር 30 ቀን 2018 ዓ.ም

ጉዳዩ፡-የገቢ ምርቶች የኢትዮጵያ ደረጃ አተገባበርን ይመለከታል
. . ከዚህ ቀደም ሲተገበር የነበረው የVOC አሰራር የስምምነት ጊዜው በመጠናቀቁ የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት አለም አቀፍ ጨረታ በማውጣት ከተመረጡት Bureau Veritas TUV Rheinland Middle East FZE: COTECNA Inspection SA World Standardization Certification & Testing Group ከተባሉ አራት አለም አቀፍ የተስማሚነት ምዘና አካላት ጋር ስምምነት በማድረግ በ13 ምርቶች ላይ ከየምርቶቹ መነሻ ሀገር የምርቶቹን ጥራት በPVOC የአሰራር ስርአት ቁጥጥር እንዲደረግ እንዲሁም የተቀሩት 17 ምርቶች ሀገር ውስጥ ከገቡ በኃላ ድርጅቱ የVerification of Conformity ስራ እንደሚያከናውን ስደቁ 4/1/61/68/18 በቀን 24/03/2018 ዓ.ም በተጻፈ ደብዳቤ እንዳሳወቃቸው ገልጸው፡፡

በሀገር ውስጥ አቅም የላብራቶሪ ፍተሻ ማድረግ የማይቻሉ በአባሪው የተገለጹትን የተመረጡ ከዉጪ ወደ ሀገር ዉስጥ የሚገቡትን 13 ምርቶችን ከመነሻ ሀገራት በPVOC አሰራር ጥራታቸዉ ተረጋግጦ እንዲላኩ ማድረግ እንዲቻል እና ፕሮግራሙ እንዲቀጥል እንዲደረግ እንዲሁም የተቀሩት 17 ምርቶች ሀገር ውስጥ ከደረሱ ቡኃላ በኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት አስፈላጊውን የVerification of Conformity ስራ በማከናወን ጥራታቸውን የማረጋገጥ ስራ የሚያከናውን ስለሆነ ለሁሉም ባንኮች መመሪያው እንዲተላለፍ አስፈላጊዉን ትብብር እንዲደረግ ጠይቀው የጉምሩክ ኮሚሽንም የጉምሩክ ሥነ-ስርዓት በሚያከናዉንባቸዉ ቅ/ጽ/ቤቶች እነዚህ ምርቶች የኢትዮጵያ ደረጃዎች ተፈጻሚነት አስፈላጊዉን ትብብር እንዲያደርግ በማሳወቅ ከዚህ ቀደም የPVOC የአሠራር ሥርዓት ሲተገበርባቸው የነበሩ ምርቶች አባሪ ተደርገው በተያያዙት ምርቶች የተተኩ መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር በደብዳቤ ቁጥር 01-1-34/1432 ሕዳር 30/2018 ዓ.ም በፃፈው ደብዳቤ ለብሔራዊ ባንክ እንዲሁም በግልባጭ ለጉምሩክ ኮምሽን እና ለባለድርሻ አካላት ገልፆል፡፡



pdf. ተያይዟል📎🤳 https://t.me/sirius_logistics/213

ለፈጣን መረጃዎች፦
Telegram 👇👇
https://t.me/sirius_logistics
https://t.me/sirius_logistics
https://t.me/sirius_logistics

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከግል እና የሶስተኛ ወገን የባንክ ሒሳብ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ ጥብቅ መመሪያ አስተላለፈየኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አደረኩት ባለው ምርመራ " ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉ...
26/10/2025

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከግል እና የሶስተኛ ወገን የባንክ ሒሳብ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ ጥብቅ መመሪያ አስተላለፈ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አደረኩት ባለው ምርመራ " ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉ የባንክ ደንበኞች በዋናነት የንግድ ድርጅቶችና ግለሰብ ነጋዴዎች ለንግድ ሥራቸው ተብሎ ከተከፈተው እና በሚመለከተው የግብር ሰብሳቢ ተቋም ካስመዘገቡት የባንክ ሒሳቦች ውጭ የግል የባንክ ሂሳባቸው ወይም የሶስተኛ ወገን የባንክ ሒሳብ ተጠቅመው የተለያዩ የንግድ ግብይቶች እና የገንዘብ እንቅስቃሴዎች እየፈጸሙ መሆናቸውን አረጋግጫለሁ " ብሏል።

" ይህ አሰራር ከግብር ሰብሳቢ ባለስልጣናት ቁጥጥርና ክትትል ለመሸሽ የሚደረግ ተግባር ከመሆኑ በተጨማሪ በዚህ አግባብ የሚፈጸሙ የፋይናንስ ግብይቶች እና የገንዘብ እንቅስቃሴዎች የወንጀል ፍሬ ወይም ሽብርተኝነትን በገንዘብ ከመርዳት ጋር የተያያዙ ወይም የተገናኙ ሊሆኑ ይችላሉ " ሲል ገልጿል።

" እነዚህን መሰል ተግባራትንም ለመግታት አስፈላጊው የተቀናጀ እርምጃ እንዲወሰድ ተወስኗል " ሲል አሳውቋል።

የፋይናንስ ሥርዓቱን ጤናማነትና ታማኝነት እንዲሁም በአጠቃላይ የኢኮኖሚ ደህንነት ለመጠበቅ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለሁሉም ባንኮች የግል ባንክ ሂሳቦችን ለንግድ እና ለሕገ-ወጥ ድርጊት የሚጠቀሙ ደንበኞችን አስመልክቶ አስፈላጊ መረጃዎችን በማደራጀት እንዲልኩ መመሪያ አስተላልፏል፡፡



ለፈጣን መረጃዎች፦
Telegram 👇👇
https://t.me/sirius_logistics
https://t.me/sirius_logistics

26/10/2025

📢📢📢
*አስመጪዎች የሐሰት ኢንቮይስ በመጠቀም ሕገወጥ ዕቃ እያስገቡ ነዉ ያለዉ ኮሚሽኑ ጥብቅ እርምጃ እንዲወስድ አስጠነቀቀ*

የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን አንዳንድ ሲል የጠራቸዉ አስመጪዎች በሕግ ከተፈቀደው በላይ የሆነ ዕቃ በሐሰተኛ ሰነድ አማካኝነት ወደ አገር ውስጥ በማስገባት ላይ መሆናቸውን አጋለጠ።

ኮሚሽኑ በጻፈው አስቸኳይ ደብዳቤ ትዕዛዝ እንደሰጠው፣ አስመጪዎች "በባንክ ፈቃድ ላይ ከተገለጸው ትክክለኛ ብዛትና መጠን ውጭ በሆነ መልኩ በኢንቮይስ (Invoice) ላይ መረጃዎችን ጨምረው በመግለጽ ሰነዶችን እያስመዘገቡ ይገኛሉ" ብሏል።

የኮሚሽኑ የኢንተለጀንስ ዳይሬክቶሬት ባደረገው ማጣራትና 18 ዲክላራሲዮኖችን በናሙና በመመርመር፣ አስመጪዎች በኢንቮይስ ላይ ጨምረው በመግለጽ እና ቀረጥ/ታክሱን በዚያው መሰረት በማስላት፣ ከሕግ ውጭ የሆነ ዕቃ በሕጋዊ ሽፋን እያስገቡ መሆኑን አረጋግጧል። ይህም የጉምሩክ ሕጎችን የሚቃረን መሆኑን ኮሚሽኑ አስታውቋል።

ይህንን ተከትሎም ኮሚሽኑ በሁሉም የጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ጥብቅ ቁጥጥር እንዲደረግ አስቸኳይ ትዕዛዝ በማስተላለፍ፣ ሕገወጥ ድርጊቱን ፈጽመው በሚገኙ አስመጪዎች፣ የጉምሩክ አስተላላፊዎች እና ባለሙያዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድ አስጠንቅቋል።

ባለሙያዎች እንደሚሉት፣ ይህ ዓይነቱ የጉምሩክ ጥብቅ ቁጥጥር ከጥቁር ገበያ የውጭ ምንዛሬ በመጠቀም ሕገወጥ ንግድ የሚፈጽሙ አስመጪዎችን ህጋዊውን መንገድ እንዲከተሉ የሚያስገድድ ነው። በመሆኑም፣ በሕገወጥ መንገድ የሚካሄደው የውጭ ምንዛሬ ፍላጎት ሲቀንስ፣ ይህ እርምጃ የውጭ ምንዛሪ ገበያው እንዲረጋጋ አስተዋጽኦ ያደርጋል ብለዋል።



pdf. ተያይዟል📎🤳 https://t.me/sirius_logistics/211

ለፈጣን መረጃዎች፦
Telegram 👇👇
https://t.me/sirius_logistics
https://t.me/sirius_logistics

24/09/2025

📢👂

ደብዳቤ ቁ፡ 4/01466/18
ቀን: ነሀሴ 30 - 2017 ዓ.ም

ጉዳዩ፡- የጉምሩክ ታሪፍ ማሻሻያን ይመለከታል፤

ስኳርን በተመለከተ በዚሁ ደብዳቤ በተራ ቁጥር 21 ላይ ከዚህ በፊት የነበረው የጉምሩክ ቀረጥ ነፃ ተሽሮ፤ በታሪፍ ደንቡ የተቀመጠው 15 በመቶ የጉምሩክ ታሪፍ ምጣኔ ተግባራዊ እንዲደረግ ታዟል::


*F

pdf. ተያይዟል📎🤳 https://t.me/sirius_logistics/204

ለፈጣን መረጃዎች፦
Telegram 👇👇
https://t.me/sirius_logistics
https://t.me/sirius_logistics

04/09/2025

የ2 ሚሊዮን ብር ዓመታዊ ገቢ ያላቸው ንግዶች ለቫት እንዲመዘገቡ ተጠየቁ

የገንዘብ ሚኒስቴር የግብር አሰባሰብ ስርዓትን ለማሻሻል ያለመ አዲስ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) መመሪያ አዉጥቷል።

በመመሪያው ቁጥር 1104/2017 መሰረት፣ ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ ዓመታዊ ገቢ ያላቸው ንግዶች እና የተወሰኑ የሙያ አገልግሎት ሰጪዎች ለቫት እንዲመዘገቡ ግዴታ ተጥሏል፡፡

በገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ የተፈረመው ይህ አዲስ መመሪያ፣ ከነሐሴ 28 ቀን 2017 ጀምሮ ተግባራዊ ሆኗል። መመሪያው ከንግድ ድርጅቶች በተጨማሪ፣ ከምድብ "ለ" ውጭ የሚመደቡ ባለሙያዎችንም ያካትታል።

እነዚህ ባለሙያዎች የዓመታዊ ገቢያቸው መጠን ምንም ያህል ቢሆን ለቫት መመዝገብ እንዳለባቸው ተመላክቷል።

በተጨማሪም መመሪያው፣ የሂሳብ መዝገብ የመያዝ ግዴታ ያለባቸው ወይም በፈቃደኝነት የሂሳብ መዝገብ የሚይዙ ሁሉም ንግዶች እንዲሁም በምድብ "ሀ" ስር የተመደቡ ግብር ከፋዮች የመመዝገብ ግዴታ እንዳለባቸው በዝርዝር አስቀምጧል።

አዲስ የተካተቱ ነባር ግብር ከፋዮች፣ መመሪያው በስራ ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በ30 ቀናት ውስጥ መመዝገብ ይጠበቅባቸዋል። ከተመዘገቡ በኋላም ለገበያ በሚያቀርቧቸው ታክስ የሚከፈልባቸው እቃዎች እና አገልግሎቶች ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ መሰብሰብ እንደሚጀምሩ ተገልጿል።



ለፈጣን መረጃዎች፦
Telegram 👇👇
https://t.me/sirius_logistics
https://t.me/sirius_logistics
https://t.me/sirius_logistics

21/08/2025

በአዲሱ የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ 1341/2016 መሠረት ወደ ታክስ መረቡ የገቡ ያለሀኪም ትዕዛዝ የሚሸጡ መድሀኒቶችን ዝርዝር፤




pdf. ተያይዟል📎🤳 https://t.me/sirius_logistics/198

ለፈጣን መረጃዎች፦
Telegram 👇👇
https://t.me/sirius_logistics

17/08/2025

❗️

የገንዘብ ሚኒስቴር፣ የደረጃ "ሀ" ግብር ከፋዮች የቅድሚያ ግብር ክፍያ ጊዜን አስመልክቶ አዲስ ማብራሪያ ሰጥቷል። ሚኒስቴሩ እንዳስታወቀው፣ የቅድሚያ ግብር የሚከፈለው በየሦስት ወሩ ሲሆን፣ የጊዜው ስሌት የሚጀምረው የሂሳብ ሪፖርት ከቀረበበት ወር ማብቂያ ጀምሮ ነው።

​ሚኒስትሩ ለገቢዎች ቢሮ የፃፈዉ ደብዳቤ ላይ ግብር ከፋዮች የየሦስት ወሩን የቅድሚያ ግብር ክፍያ፣ የሂሳብ ሪፖርት ካቀረቡበት ወር በኋላ ባሉት በየሦስት ወሩ መጨረሻ ባሉት 30 ቀናት ውስጥ መፈጸም ይጠበቅባቸዋል።

​በዚህ ማብራሪያዉ ላይ እንደጠቆመዉ የሂሳብ ሪፖርታቸውን በጥቅምት ወር የሚያቀርቡ ግብር ከፋዮች፣ የመጀመሪያውን ቅድሚያ ግብር በየካቲት ወር፣ ሁለተኛውን በግንቦት ወር፣ ሦስተኛውን ደግሞ በነሐሴ ወር ይከፍላሉ። በተጨማሪም፣ ዓመታዊ ግብራቸውን አጠቃለው እስከ ጥቅምት ወር መጨረሻ ድረስ መክፈል እንደሚኖርባቸው በዝርዝር አስቀምጧል።

ይህን ተከትሎ ​ የሂሳብ ሪፖርት የሚቀርብበት ወር የግብር ክፍያ ማጠናቀቂያ ወር እንደሚሆን የገለፀ ሲሆን በዚህም መሰረት፣ አንድ ግብር ከፋይ በየሦስት ወሩ የከፈለው ቅድሚያ ግብር ከጠቅላላ ዓመታዊ ግብሩ ያነሰ ከሆነ፣ የቀረውን ልዩነት መክፈል ግዴታ እንዳለበት አፅንኦት ሰጥቷል።



ለፈጣን መረጃዎች፦
Telegram 👇👇
https://t.me/sirius_logistics

15/08/2025

📢🚫👂

ደብዳቤ ቁ፡ 4-0/0147/18
ነሀሴ 08 ቀን 2017 ዓ.ም

ጉዳዩ፦ የሲኖትራክ ተሽከርካሪ ወደ አገር እንዳይገባ የተጣለ እግድን አስመልክቶ መረጃ ስለመስጠት፤



pdf. ተያይዟል📎🤳 https://t.me/sirius_logistics/196

ለፈጣን መረጃዎች፦
Telegram 👇👇
https://t.me/sirius_logistics

15/08/2025

*ደንብ ቁጥር 574/2017 የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ ንግድ ቀጠና ስምምነት የዕቃዎች ቀረጥ መጣኔ ቅነሳ ማስፈጸሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ*

REGULATION No. 574/2025 COUNCIL OF MINISTERS REGULATION FOR THE IMPLEMENTATION OF THE CONCESSION OF DUTY TARIFF RATES ON GOODS FOR THE AFRICAN CONTINENTAL FREE TRADE AREA



pdf. ተያይዟል📎🤳 https://t.me/sirius_logistics/195

ለፈጣን መረጃዎች፦
Telegram 👇👇
https://t.me/sirius_logistics

14/08/2025

*የገቢ ግብር (ማሻሻያ) አዋጅ ቁጥር 1395/2017፤*

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሐምሌ 10 ቀን 2017 ዓ.ም ባካሄደው 2ኛ አስቸኳይ ስብሰባ በተዘጋጀው የፌዴራል የገቢ ግብር (ማሻሻያ) አዋጅ ቁጥር 1395/2017 ሆኖ በስራ ላይ እንዲውል ያፀደቀው መሆኑን እና አዋጁ በምክር ቤቱ ከፀደቀበት ሐምሌ 1 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በስራ ላይ እንዲውል የተወሰነ ሲሆን የአዋጁ መግለጫ፣ የአማርኛና እንግሊዝኛ ቅጅ 51 ገጽ ከታች ተያይዟል፡፡



pdf. ተያይዟል📎🤳 https://t.me/sirius_logistics/194

ለፈጣን መረጃዎች፦
Telegram 👇👇
https://t.me/sirius_logistics

Address

Dire Dawa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Sirius Transit and Logistics Service posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Sirius Transit and Logistics Service:

Share