Ministry of Education Ethiopia

Ministry of Education Ethiopia This is FDRE ministry of education official page.we are promoting Education Achievement&Attainement

ፔፕ ጋርዲዮላ የካራባዎ ዋንጫን 5 ጊዜ ያነሳ ብቸኛው አሰልጣኝ ሆኗል***************ዛሬ በተደረገው የካራባዎ ዋንጫ ፍጻሜ ማንችስተር ሲቲ አርሰናልን 2 ለ 0 በማሸነፍ ዋንጫውን ወስዷ...
22/03/2026

ፔፕ ጋርዲዮላ የካራባዎ ዋንጫን 5 ጊዜ ያነሳ ብቸኛው አሰልጣኝ ሆኗል
***************

ዛሬ በተደረገው የካራባዎ ዋንጫ ፍጻሜ ማንችስተር ሲቲ አርሰናልን 2 ለ 0 በማሸነፍ ዋንጫውን ወስዷል፡፡

ስፔናዊው አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ይሄንን ዋንጫ 5 ጊዜ በማንሳት ብቸኛው አሰልጣኝ የሆነበትን አዲስ ታሪክ ጽፏል፡፡

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ 20ኛው ዙር የተማሪዎችን ምረቃ መርሀ-ግብር።***//***መጋቢት 13/2018 ዓ/ም በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ለመጀመሪያ...
22/03/2026

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ 20ኛው ዙር የተማሪዎችን ምረቃ መርሀ-ግብር።
***//***

መጋቢት 13/2018 ዓ/ም

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ለመጀመሪያ ጊዜ በሰብ-ስፔሻሊቲ ፕሮግራም ያስመረቃቸውን ጨምሮ በሕክምና ስፔሻሊቲ፣ በሕክምና ዶክትሬት ዲግሪ እና በሌሎች የጤና ሳይንስ ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 249 ወንዶች እና 178 ሴቶች፣ በአጠቃላይ 427 የጤና ባለሙያዎችን ዛሬ በደማቅ ሥነ-ሥርዓት አስመርቋል።

የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊና የዕለቱ የክብር እንግዳ ክብርት ዶ/ር ሰላማዊት መንገሻ ለተመራቂ ተማሪዎች ባስተላለፉት መልዕክት ትምህርት ለሀገር ዕድገትና ብልጽግና መሠረት መሆኑን ጠቁመው በተለይም መንግሥት በጤናው ዘርፍ ለሚሰጠው ልዩ ትኩረት ተመራቂዎች የድርሻቸውን ለመወጣት ዝግጁ መሆን እንደሚጠበቅባቸው ገልጸዋል። የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጁ ኮምፕርሔንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የሲዳማና የአጎራባች ክልሎች ኩራት መሆኑን የገለጹት ዶ/ር ሰላማዊት፣ ዩኒቨርሲቲው በየዓመቱ የሚያስመርቃቸው ባለሙያዎች በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የጤናውን ዘርፍ በብቃት እያገለገሉና እየመሩ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ችሮታው አየለ በመክፈቻ ንግግራቸው የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በመማር ማስተማር፣ በምርምርና በማህበረሰብ አገልግሎት ስኬታማ ከሆኑ የዩኒቨርሲቲው ኮሌጆች መካከል አንዱ መሆኑን ጠቅሰው ዩኒቨርሲቲው በያዝነው አመት ለሚያከብረው የ50ኛ አመት የወርቅ ኢዮቤልዩ በአልና የራስ ገዝነት ሽግግር በልዩ ሁኔታ ዝግጅት መደረጉን ተናግረዋል። ኮሌጁ ብቁ የጤና ባለሙያዎችን ከማፍራት ባሻገር በሆስፒታሉ የሚሰጣቸውን የህክምና አገልግሎቶች በቴክኖሎጂና ዲጂታላይዜሽን ለማዘመን የማስፋፍያ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል።

የኮሌጁ ቺፍ ኤግዘክዩቲቭ ዳይሬክተር ዶ/ር ፍፁም ወ/ገብርኤል በበኩላቸው የሕክምና ትምህርት በአለም አቀፍ ደረጃ ፈታኝና ከፍተኛ ትጋትን የሚጠይቅ መሆኑን ጠቁመው ተመራቂዎቹም ትምህርቱ የሚጠይቀውን ዋጋ ከፍለው ለቤተሰቦቻቸውና ለሀገራቸው ኩራት ለመሆን ለዚች ቀን ስለደረሱ በራሳቸው ሊኮሩ እንደሚገባና ያስተማረቻቸውን ሃገር ዜጎች በሙያቸው የላቀ አገልግሎት ለመስጠት እንዲዘጋጁ አደራ ብለዋል። ዶ/ር ፍጽም ኮሌጁ በኮምፕሪሔንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሪፈራል ሆስፒታሉ አማካይነት በዓመት ከ20 ሚሊዮን በላይ ለሚሆን የህብረተሰብ ክፍል የካንሰር ጨረር ሕክምና፣ የፎረንሲክ ምርመራ፣ የስነ-ምረዛ እና የጨቅላ ሕጻናት ሕክምናን ጨምሮ የልህቀት ማዕከል ለመሆን እየሠራ መሆኑን አመላክተዋል።

በህክምና ዶክትሬት ዲግሪ ከፍተኛውን ውጤት (CGPA 3.76) በማስመዝገብ የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ የሆነው ተመራቂ ዶ/ር ኤፍሬም ብዙአየሁ እንዲሁም ከጤና ሳይንስ ፕሮግራሞች CGPA 3.96 በማስመዝገብ የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚው ኦስማን መዲድ፣ እና ከሴቶች በህክምና ዶክትሬት ዲግሪ ከፍተኛውን ውጤት CGPA 3.55 በማስመዝገብ የተመረቀችው ዶ/ር ሔርሜላ ገዛኸኝ፣ ከአጠቃላይ የትምህርት ፕሮግራሞች ከፍተኛ ውጤት ያመጡ ሴት ተማሪዎችን ጨምሮ ከዕለቱ የክብር እንግዶች እጅ ሽልማታቸውን ተቀብለዋል።

ተመራቂዎች በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ! እንኳን ደስ አለን!

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ
ሁሌም ለልህቀት!

🗓 የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና መስጫ ትክክለኛ ጊዜው ገና ባይጸድቅም ፈተናው ሰኔ ውስጥ እንደሚሰጥ ተጠቁሟል !የትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች አገልግሎት የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ምዝ...
21/03/2026

🗓 የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና መስጫ ትክክለኛ ጊዜው ገና ባይጸድቅም ፈተናው ሰኔ ውስጥ እንደሚሰጥ ተጠቁሟል !

የትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች አገልግሎት የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ምዝገባ መጋቢት 15 ቀን 2018 ከቀኑ 11 ሰዓት 30 እንደሚጠናቀቅ፣ ያልተመዘገበ እንደማይፈተን በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል አሳስቧል።

በጀት ከተመደበ፣ ፈተና አስፈጻሚዎች ከተሰማሩ በኋላ አዲስ ተመዝጋቢ ቢቀርብ ለማስተናገድ እንደሚቸገሩ አስረድተዋል። ትክክለኛ ጊዜው ገና ባይጸድቅም ፈተናው ሰኔ ውስጥ እንደሚሰጥ ጠቁመዋል።

ተመዝጋቢዎች ከ9 እስከ 11 የተማሩበት ውጤት ሊኖራቸው እና አሁን ላይ 12ኛ ክፍል እየተማሩ ሊሆኑ እንደሚገባ ገልጸዋል። ድጋሚ ለሚፈተኑ ደግሞ 750 ብር ክፍያ በመፈጸም ከዚህ በፊት የተፈተኑበትን አድሚሽን ካርድ ማስገባት፣ https://register.eaes.et ላይ መመዝገብ እንዳለባቸው አሳስበዋል።

ይህም 150 ብሩ ለምዝገባ፣ ለእያንዳንዱ ስድስት ፈተና 100 ብር ተደርጎ ተሰልቶ፣ ተፈታኞች " ቢያንስ ኮስት ሸር " እንዲያደርጉ እና " ከፍዬ ነው " በሚል ለፈተናው ትኩረት እንዲሰጡ ታስቦ የተወሰነ መሆኑን ገልጸዋል።

ተፈታኞች በመረጡበት የፈተና ማእከል መፈተን እንደሚችሉ ያስረዱት እሸቱ (ዶ/ር)፣ " ለምሳሌ አምና አርባምንጭ የተፈተነ ተማሪ፣ ዘንድሮ ወደ አዲስ አበባ መጥቶ ከሆነ ለመፈተን አርባምንጭ መሄድ ሳይጠበቅበት አዲስ አበባ ካሉ ትምህርት ቤት አንዱን መርጦ የግል ተፈታኝ ሆኖ ይፈተናል " ብለዋል።

የዜናው ምንጭ: ቲክቫህ ኢትዮጵያ

ለሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ማህብረሰብ በሙሉ***//***መስከረም 18/2018 ዓ/ምሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ 22ኛዉን አለም አቀፍ የአትዮጵያ ጥናት ጉባኤ ከነገ መስከረም 19-23/2018 ዓ/ም ለማስተናገድ ...
29/09/2025

ለሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ማህብረሰብ በሙሉ
***//***
መስከረም 18/2018 ዓ/ም

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ 22ኛዉን አለም አቀፍ የአትዮጵያ ጥናት ጉባኤ ከነገ መስከረም 19-23/2018 ዓ/ም ለማስተናገድ አስፈላጊውን ዝግጅት አጠናቆ ከዓለም ዙርያ የሚመጡ የጉባዔዉ ተሳታፊ እንግዶቹን ለመቀበል ተዘጋጅቷል፡፡

ይህንን ታሪካዊ አለምዓቀፍ ጉባኤ ለማዘጋጀት ያለፉትን ሁለት ዓመታት ከሚመለከታቸዉ ባለድርሻ አካላትና አጋሮች ጋር በመሆን ዘርፈ ብዙ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ተሰርተዋል፡፡

የዝግጅት ምዕራፎቹንም የዩኒቨርሲቲዉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በየወቅቱ እየገመገሙ ለአዘጋጅ ኮሚቴዉና ለሚመለከታቸው የሥራ ክፍሎች አቅጣጫ ሲሰጡ ቆይተዋል፡፡ ጉባኤው የሚካሄድበት የአፍሪካ ህብረት አዳራሽም ለመስተንግዶ ዝግጁ ሆኗል::

እንግዶቻችን ከዛሬ ጀምሮ ወደ ሐዋሳ የሚገቡ ይሆናል:: ስለሆነም እንግዶች ጉባዔዉ በሚካሄድበት ወቅት በዩኒቨርሲቲዉ ግቢ ዉስጥና በከተማዉ የሚያሳልፉት ጊዜ መልካም ገፅታ ይዘው እንዲመለሱ ለማስቻል ከሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጋር በመተባበር አስፈላጊዉ የቅንጅት ሥራዎች ተሰርተዋል፡፡

ዉድ የዩኒቨርሲቲያችን መምህራን፣ የአስተዳደር ሰራተኞች፣ ተማሪዎች እና የሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎች:-

እነዚህን ለቀጣይ አምስት ቀናት በዩኒቨርሲቲያችንና በከተማችን የሚቆዩትን ከሀገር ዉስጥና ከሀገር ዉጪ የሚመጡ በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ የሚመራመሩ ዓለም አቀፍ ምሁራን፣ የተለያዩ ሀገራት ዲፕሎማቶች፣ የፌደራልና የክልል የመንግስት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና አጋሮች በፍጹም ኢትዮጵያዊ ጨዋነትና የሲዳማ ባህላዊ እንግዳ ተቀባይነት ሥነ-ምግባር እንግዶቹን በመቀበልና በማስተናገድ የተለመደዉን ትብብር እንዲታደርጉ ዩኒቨርሲቲዉ ጥሪዉን ያስተላልፋል፡፡

የእነዚህ እንግዶች ወደ ዩኒቨርሲቲያችንና ከተማችን መምጣት የዩኒቨርሲቲያችንንም ሆነ የከተማችንን ብሎም የክልሉን ከፍ ብሎ ደግሞ የኢትዮጵያን በጎ ገጽታ የሚገነባ፣ የዕዉቀት ሽግግርን የሚፈጥር፣ ትብብርን የሚያበረታታ እንዲሁም የባህል ልዉዉጥ እና ቱሪዝምን የሚያጎለብት ብሎም ምጣኔ ሃብታዊ አበርክቶ ያለዉ ለበርካቶች ምቹ አጋጣሚ መሆኑን ለማስታወስ እንወዳለን፡፡

በዚህ አጋጣሚ ለዚህ ጉባዔ ዝግጅት አስተዋጽኦ እያደረጉ ያሉትን ሁሉንም ባለድርሻ እና አጋር አካላት ዩኒቨርሲቲያችን ከልብ ያመሰግናል፡፡

ለበለጠ መረጃ ከታች ያለዉን ማስፈንጠሪያ በመጫን የጉባዔዉን ድረ-ገጽ እንድትጎበኙ እንጋብዛለን፡፡

https://ices22.hu.edu.et/

ዶ/ር ችሮታዉ አየለ (የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ተ/ፕሬዚዳንት)
ዶ/ር ታፈሰ ማቲዎስ (የምርምርና ትብብር ም/ፕሬዚዳንት)
ፕሮፌሰር ተስፋዬ ሰመላ (የ22ኛዉ አለም አቀፍ የአትዮጵያ ጥናት ዓለምአቀፍ ጉባኤ አዘጋጅ ኮሚቴ ሰብሳቢ)

ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በውጭ ሀገር ካሉ አቻ ተቋማት ጋር የሚያደርጓቸውን ስምምነቶች አፈጻጸም አጠናክረው እንዲቀጥሉ ተጠየቀ፤ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትም...
22/08/2025

ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በውጭ ሀገር ካሉ አቻ ተቋማት ጋር የሚያደርጓቸውን ስምምነቶች አፈጻጸም አጠናክረው እንዲቀጥሉ ተጠየቀ፤

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ አስተባባሪነት ኢንሃ ከተሰኘ የኮሪያ ዩኒቨርሲቲ ጋር በትብብር ለመስራት የሚያስችል የጋራ መግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራረሙ

=================================

(ነሃሴ 16/2017 ዓ.ም) በስምምነት ፊርማ ስነ-ስርዓቱ ላይ የትብብር ስምምነቱ በአቬሽን ሳይንስ፣ ኤሮስፔስ ኢንጂነሪንግ እና ስማርት ሲቲ ትምህርት ፕሮግራሞችን በማጠናከር እንደሆነም ተገልጿል።


ዩኒቨርሲቲው በሀገራችን የአቬሽን ሳይንስ እና ኤሮስፔስ ኢንጂነሪንግ ትምህርት ፕሮግራሞችን ለማጠናከር ከጅማ ዩኒቨርሲቲ ጋር በትብብር ለመስራት የመግባቢያ ሰነዱን የተፈራረመ ሲሆን ኢንሃ ዩኒቨርሲቲን በመወከል ፕሮፌሰር ሂቸንግ ኮህ እና ጅማ ዩኒቨርሲቲን በመወከል ደግሞ አቶ ኤፍሬም ዋቅጅራ ተፈራርመዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው በሀገራችን የስማርት ሲቲ ትምህርት ፕሮግራምን ለማጠናከር ከአዲሰ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ጋር የመግባቢያ ሰነዱን የተፈራረመ ሲሆን አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲን በመወከል የዩኒቨርስቲው አካዳሚክ ምክትል ፕሬዝዳንት የሆኑት ዶ/ር ከማል ኢብራሂም ተፈራርመዋል፡፡

የመግባቢያ ሰነዶቹ የሚያተኩሩባቸው ቁልፍ ጉዳዮች የአቅም ግንባታ ሥልጠና፣ ምርምር እና የተማሪዎችና መምህራን ልውውጥ ከትብብር ማዕቀፎቹ መካከል ዋና ዋናዎቹ እንደሚሆኑም ተገልጿል።


የማፈራረም ሂደቱን የመሩት በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሹኔ የትብብር ማዕቀፎቹ በሶስቱም የትምህርት ፕሮግራሞች ሀገራችን ብቁ ባለሙያዎችን እንድታፈራ ከፍተኛ አስተዋጽኦ የሚያበረክቱ መሆናቸውን ጠቁመው ተቋማቱ በስምምነቱ መሰረት ለውጥ ለማምጣት ጠንክረው መስራት ይኖርባቸዋል ብለዋል።

ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው አክለውም ሶስቱም ተቋማት ተቋሞቻቸውን በመወከል የወሰዱትን የጋራ ሀላፊነትና አደራ በሚገባ እንደሚወጡ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል፡፡

ሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያ መነጋገሪያ ስለሆነችው ብርቱካን ተመስገን ከበደ ከትምህርት ሚኒስቴር የተሰጠ ማብራሪያሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያ መነጋገሪያ ስለሆነችው ብርቱካን ተመስገን ከበደ ከከፍተኛ...
28/03/2025

ሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያ መነጋገሪያ ስለሆነችው ብርቱካን ተመስገን ከበደ ከትምህርት ሚኒስቴር የተሰጠ ማብራሪያ

ሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያ መነጋገሪያ ስለሆነችው ብርቱካን ተመስገን ከበደ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር ግንኙነት ስላለው ማብራሪያ መስጠት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል።

በስም ተጠቃሽ በ2012 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ተማሪ የነበረች ቢሆንም የብሄራዊ ፈተናው በወቅቱ በተፈጠረው ዓለም ዓቀፍ የኮቪድ ወረርሽኝ ምክንያት ከየካቲት 29 እስከ መጋቢት 02/2013 ዓ.ም እንዲሰጥ መደረጉ ይታወሳል። ተማሪዋም በዚሁ ጊዜ በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት፣ በምስራቅ ጎጃም ዞን በሞጣ መሰናዶ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ፈተና ወስዳ 392 ውጤት በማምጣት በ2013 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ምደባ ተደርጎላታል፡፡ ሆኖም ግን ወደተመደበችበት ዩኒቨርሲቲ ያልሄደችና ያልተመዘገበች ሲሆን ወደ ሀዋሳ ከተማ በማቅናት በተከታታይ የትምህርት ኘሮግራም (ኤክስቴንሽን) ተመዝግባ “በአካውንቲንግና ፋይናንስ” የትምህርት ክፍል በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ ዲግሪ ኘሮግራም ከግቢ ውጭ ሆና ትምህርቷን ስትከታተል የነበረችና ትምህርቷንም ሳትጨርስ ያቋረጠች መሆኑን ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የተገኘ መረጃ ያረጋግጣል፡፡

በተቃራኒው በኢቢኤስ ቴሌቪዥን ስርጭት በተላለፈው ፕሮግራም ግለሰቧ በሀሮማያ ዩኒቨርስቲ ተመድባ ወደ ሀሮማያ በመጓዝ ላይ ሳለች አውቶቡስ ውስጥ ባገኘቻት ደምቢደሎ ዩኒቨርስቲ ተመድባ በመጓዝ ላይ ካለች ሌላ ተማሪ ጋር በመነጋገር ሀሮማያ ዩኒቨርስቲ የነበራትን ጉዞ በመሰረዝ ወደ ደምቢደሎ ዩኒቨርስቲ ሄዳ ለመማር ተመዝግቢያለሁ ማለቷ ከእውነታውና ከአሰራር ውጭ የሆነና በፍጹም ወደ ደምቢደሎ ዩኒቨርስቲ ያልሄደችና ምዝገባም ያላደረገች መሆኑ የዩኒቨርስቲው መረጃ ያስረዳል። በዚህ አጋጣሚ ማንኛውም አይነት የአዲስ ተማሪዎች ምደባ የሚከናወነው በትምህርት ሚኒስቴር ብቻ እንጂ በዩኒቨርስቲዎች ደረጃ የማይፈቀድ መሆኑም ለማሳዎቅ እንወዳለን።

በመሆኑም፤

1. በማህበራዊ ሚዲያው እየተሰራጩ ያሉ መረጃዎች በከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ ጋር ካለው እውነታ ውጪ የሆነ መሆኑን እንገልጻለን፤ ይህንኑ የሚያረጋግጡ መረጃዎችም ከዚህ ማብራሪያ ጋር ተያይዘዋል፤


2. ይህንን የተሳሳተ መረጃ መሰረት በማድረግ በውስን ዩኒቨርሲቲዎች የመማር ማስተማር ስራውን ለማስተጓጎል የተለያዩ ሙከራዎች ተደርገዋል፡፡ እንደሚታወቀው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመማር ማስተማር፣ የምርምርና የማህበረሰብ አገልግሎት ስራዎች የሚከናወኑባቸው፣ እውቀትና እውነት የሚሰርጽባቸው በእውነትና በእውቀት የሚመሩ አለም ዓቀፍ ተቋማት መሆናቸው ሊታዎቅ ይገባል።

3. የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ሰርቪስ (EBS) ከዚህ ቀደም እንደሚያደርገው እንደማንኛውም ሚዲያ ጉዳዩን ከማሰራጨቱ በፊት ከዩኒቨሲቲዎቹ ወይንም ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘውን መረጃ ማጣራት ሲገባው ይህንን ጉዳይ ሳያጣራ በቀጥታ አየር ላይ ማዋሉ ህዝቡን ከማሳሳት ባሻገር የዩኒቨርስቲዎቹን ገጽታ በማበላሸትና በማጠልሽት ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰ በመሆኑ ሃላፊነቱን ሊወስድ ይገባል።

ስለሆነም እንደዚህ አይነት የፈጠራና የሀሰት ቅንብሮችን መሰረት አድርጎ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ የሚደረግ የመማር ማስተማር እንዲሁም የምርምር ስራዎቻቸውን ሊያውኩ የሚችሉ ማንኛውም አይነት እንቅስቃሴና ተግባር ፍፁም ተቀባይነት የሌላቸውና ይህንንም ሆን ብለው በሚፈጽሙና በሚገፉ አካላት ላይ ከፍተኛ አሰተዳደራዊ እርምጃ አለፍ ሲልም በተቋማቱ ንብረትም ሆነ በሰው ላይ ለሚደርስ አደጋና ጉዳት ህጋዊ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ማሳሰ

16/10/2024
ተማሪ ሩት መርሻ በአሰቃቂ ሁኔታ ሞታለች😭በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የቢዝነስ ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ የቱሪዝም ትምህርት ክፍል ሁለተኛ አመት ተማሪ የነበረችው ተማሪ ሩት መርሻ ከጓደኛዋ ጋር በተፈጠረ...
16/10/2024

ተማሪ ሩት መርሻ በአሰቃቂ ሁኔታ ሞታለች😭

በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የቢዝነስ ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ የቱሪዝም ትምህርት ክፍል ሁለተኛ አመት ተማሪ የነበረችው ተማሪ ሩት መርሻ ከጓደኛዋ ጋር በተፈጠረው አለመግባባት ከሦስተኛ ፎቅ ገፍትሯት ተፈጥፍጣ ማረፏ ተሰምቷል።

ጓደኛዋ ገዳዩ በወላይታ ዞን ፖሊስ ቁጥጥር ሥር ተይዞ ይገኛል።

ነፍስሽ በሰላም ትረፍ😭

በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና 5.4 በመቶ ተማሪዎች 50 በመቶና በላይ ውጤት ማስመዝገባቸው ተገለጸ።     ----------------------------------------...
09/09/2024

በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና 5.4 በመቶ ተማሪዎች 50 በመቶና በላይ ውጤት ማስመዝገባቸው ተገለጸ።
-------------------------------------------------
የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤትን አስመልክቶ የትምህርት ሚኒስትሩ ክቡር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

ሚኒስትሩ እንደገለጹት ለአገር አቀፍ ፈተና ከተቀመጡ 674,823 ተማሪዎች ውስጥ 36, 409 ወይም 5.4 በመቶ የማለፊያው ውጤት ማግኘታቸውን ገልጸዋል። የማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ቁጥር ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ጊዜ በ9,114 ተማሪዎች ብልጫ እንዳለውም ተናግረዋል።

በዚህም በተፈጥሮ ሳይንስ 28,158 ወይም 9 በመቶ በማህበራዊ ሳይንስ 8,251 ወይም 2 በመቶ የማለፊያ ውጤት ማምጣታቸውን አመላክተዋል።

በፈተናው 1,221 ተማሪዎች ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገባቸውን የገለጹ ሲሆን በባለፈው ዓመት ከተመዘገበው 220 አንጻር የተሻለ ውጤት መሆኑም ተገልጿል። ቀደም ሲል በነበረው የመሰናዶ ትምህርት በትግራይ ክልል ፈተናቸውን ከወሰዱ ተፈታኞች መካከል ከ700 በተፈጥሮ ሳይንስ ከትግራይ ቀላሚኖ ት/ቤት አንድ ተማሪ 675 ማስመዝገቡን ገልጸዋል።

በተመሳሳይ በዚህ ዓመት ፈተናቸውን ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል ከ600 በተፈጥሮ ሳይንስ ከአዲስ አበባ አግዚሊየም ካቴድራል ት/ቤት 575 (በሴት ተማሪ) በማህበራዊ ሳይንስ ከአዲስ አበባ ኢትዮ ፓረንትስ 538 (በሴት ተማሪ) ከፍተኛ ውጤት መመዝገቡን ተናግረዋል ።

በዚህ ዓመት ሁሉም ክልሎችና ከተማ መስተዳድሮች ከአምናው በተሻለ ተማሪዎችን ማሳለፋቸውን የገለጹት ሚኒስትሩ 1,363 ት/ቤቶች ግን ምንም ተማሪ አለማሳለፋቸውን ጠቁመዋል።

ክቡር ሚኒስትሩ በመጨረሻም 50 በመቶና በላይ ያመጡት በቀጥታ ወደ ዩኒቨርሲቲ እንደሚገቡ ጠቅሰው የተወሰኑ ተማሪዎችም በሪሜዲያል ፕሮግራም ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ተናግረዋል።

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ministry of Education Ethiopia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share