Visit Gurage

Visit Gurage ሠላም ቤተሰቦች በዞናችን:በአካባቢያችን ያሉን ታሪካች ለአለም የምናሳይበት የfacebook ገፅ ነው Share follow like እንዲሁም invent በማረግ እንተባበር

05/03/2024

በቀላሉ በስልካቹሁ ገንዘብ ስሩ እመኑኝ ስሩበት

05/11/2022
21/08/2022
20/08/2022
19/08/2022

ከምሁር አክሊል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተወካይ ክቡር Bartema Fikadu ለመላው ጉራጌ ህዝብ የተላለፈ ኮስተር ያለ ጥሪ!!
👇
የሚገርመው ብልጽግና ፓርቲ ከሰሜኑ ጦርነት መነሻ በማድረግ ወደለየለት አምባገነን ወታደራዊ መንግስት ሆኗል።ለኢትዮጵያውያን የገባው ቃል ሽሯል።ከወያኔም ከደርግም የባሠበት አፋኝ ሆኗል።በኦሮሚያ ክልል በወለጋ፣በጉጂናበሸዋ ከፍተኛ የሰው እልቂት እያለ የተዘገጀ ሠራዊት እያለው ከማንድፖስት ለማቋቋምናአሸባሪን ለመመከት ሲያቅማማ ምድሩ በደም አጨማለቃት ህዝብ አልቆ የሀገሪቱ ህዝብ ሲቆጣ በህዝብ ግፊት ወደወለጋ ጦር አዘመተ።ምንም ችግር በሌለበት በዴሞክራሢያዊና በሠላማዊ መንገድ ጥያቄ ላቀረበ ህዝብ በሬ ለመከለከያ ለአራተኛ ዙር ለጫነ የጉራጌዞን ህዝብ በነፍጥ ማሥፈራራት የለየለት ወታደራዊ አምባገነንት ነው።የዞኑ ምክር ቤት የወሰነው በክልል መደራጀት የ3 አመት ጥያቄ ለማፈን ክላስተር ቢቀርብለትም በአብላጫ ድምፅ ውድቅ ያደረገው ሀሣብ ዳግም ለውይይት ለመጋበዝ፤የክላስተር ፍላጎት ያላቸው ዞኖቸ ስልጤ፣ ሃላባ ፣ሀዲያናከምባታ እንዲሁም የም ማደራጀትና ህዝበ ውሳኔ መሥጠት ሲገባ በነበረበት ማለት" ዶሮ ሲያታልሏት በመጫኛ ጣሏት " ነው የሆነው።ይህ ደግሞ የከፋ ወታደራዊ አምባ ገነንነት ነው።እናውቃለን ለመከላከያ ፌደራልፖሊስና ለፀጥታ ሃይሎችጉራጌ ክብር አለው።ዛሬም ነገም ክብር አለው ህገመንግስታዊ መብቱ መጣስ ግን ዋጋ ያሥከፍላል።የሚፈልገው ሪፈረንደም ነው ።ጠቅላዩ ወታደር ናቸው ለዚህም ነው አምባገነን የሚሆኑት በመጨፍለቅ በመዝለፍ በማሥፈራራት ረዥም የሥልጣንጊዜ የሚወስዱት።የፌደሬሽን ምክር ቤትአባላት ማለት የዞን አስተዳዳሪዎች፣የክልል አመራሮችና የክልልምክር ቤት አባላት ናቸው።ታዲያከአለቃቸው ትእዛዝ እንዴትስ ይወጣሉ? ህገመንግስቱ እራሳቸው ጥሰው ሌላውን ለማፈኛ ህገመንግሥታዊ ስረአቱ በሀይል ለመጣሥ ተሞክሯል ይላሉ። የማያፍር የ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን አፋኝ ቡድን። ጉራጌ ስትከፋፈል ትጠቃለህ አንድ ስትሆን ታሸንፋለህ።አንድነትህ ባለሥልጣናት ኤኔትሬ የኢህአዲግ ካድሬ ለአንተ የእግር እሳት የሆኑ የጎረቤት ዞን አመራሮች ሀሣብ አትሙላላቸው።ከመቼም በላይ አንድነትህ ያዋጣሃል።ጉራጌከክልል በላይ ነው። ይበቃል አሁን ኧሁኛን ዋማርድ !!!

03/08/2022

የጉራጌ ህዝብ ህገ- መንግስታዊ መብቱን እንዲያገኝ ለምትታገሉ ሁሉ 📢

💎 ጥያቄያችንን እያቀረብን ያለነው በሠላማዊና በህጋዊ መንገድ ነው። በፍፁም የሀይል ቃላቶችን እና አላስፈላጊ ንግግሮችን እንዳትጠቀሙ። ቢሰድቧችሁ እንኳን መልሳችሁ እንዳትሳደቡ።

💎 የየትኛውንም አመራር ፎቶ ለጥፋችሁ አትሳደቡ።

💎 ጉራጌ ህገ- መንግስታዊ መብቱን በመጠየቁ በተሳሳተ መንገድ ለሚፅፉ ገፆች ከተቻለ በጨዋ ደምብ ማስረዳት። ሆን ብለው ከሆነ ደግሞ መልስ ባለመስጠት ከጨዋታ ውጪ ማድረግና ትኩረት ማሳጣት።

💎 ሰሞኑን ፌክ አካውንቶች በብዛት ተከፍተዋል። የእነኚህ ፌክ አካውንቶች ዋና አላማ የጉራጌ ማህበረሰብ በሰላማዊ መንገድ የጠየቀውን በክልል የመደራጀት ህገ- መንግስታዊ መብት ለማደናቀፍ ሆን ብለው የጥላቻ ንግግር የሚያስተላልፉ ቡድኖች መኖራቸውን በመገንዘብ 👉 ለፌስቡክ ሪፖርት በማድረግ ገፆቹን
ማዘጋት ካልሆነም እድሜ ለዙከንበርግ Block! ማድረግ። ለሌሎች መማሪያ (ለማስረዳት) ይጠቅማል ብላችሁ እስካላመናችሁ ድረስ በፍፁም መልስ አትመልሱ።

💎 የፌክ አካውንቶቹ ባህሪ ደግሞ ከጉራጌ ማህበረሰብ ጋር አብረው ተዋልደውና ተዋደው የሚኖሩ ማህበረሰብ ወንድም እህቶቻችን ተቆርቋሪ በመምሰል የሚፃፉ መሆኑን በደምብ መረዳት ያስፈልጋል።

💎 ጥያቄያችን የጉራጌ ማህበረሰብን ስነ- ልቦና በሚመጥን እና ኢትዮዽያዊ ጨዋነታችንን በተላበሰ መልኩ ብቻ መሆን ይኖርበታል።

💎 የእራሳችንን መብት ለማስከበር እንደምንታገለው ሁሉ የሌሎችንም መብትና ጥያቄ ማክበር ግዴታችን ብቻ ሳይሆን ባህላችንም ጭምር መሆኑን አንዘንጋ ።

💎 ማህበራዊ ሚዲያ ላይ አቅጣጫ ማስቀየሻ የተለያዩ አጀንዳዎች ስለሚፈበረኩ አይናችሁን ከክልል ጥያቄ ላይ አትንቀሉ። የማይመለከታችሁ ጉዳይ ላይ አስተያየት አትስጡ። ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ አለማለቴ ይሰመርበት!

💎 በክልል የመደራጀት ህገ- መንግስታዊ መብታችንን እየጠየቅን እንጂ መንግስትን እየተቃወምን ወይም ሌላ የፖለቲካ አጀንዳ እያራመድን ባለመሆኑ ወደ ሌላ የፖለቲካ አቅጣጫ ሊጠመዝዙን ለሚፈልጉ ሀይሎች መጠቀሚያ እንዳንሆን ጥንቃቄ እናድርግ።

💎 ጉራጌ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የሚለውን ሎጎ በተለያዩ ተነባቢ ገፆች ላይ ያጋሩ።

💎 ሁሉም ነገር ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ስለማይፃፍ የምናስተላልፋቸው መልዕክቶች ላይ ጥንቃቄ እናድርግ።

👉 የማንጨርሰውን አልጀመርንም‼



31/07/2022

በዚምባብዌ በአንድ ወቅት በተፈፀመ የባንክ ዘረፋ ጭምብል አጥልቀው የመጡ የዘራፊዎቹ መሪ "እንዳትንቀሳቀሱ ገንዘቡ የሀገሪቱ ነው ነፍሳችሁ ደግሞ የግላችሁ ነች" በማለት አስጠነቀቀ..!!!

በባንኩ የሚገኝ ሁሉም ሰው መሬት ላይ ተደፋ። ይህ "Mind Changing concept" ይባላል። የሰዎችን አእምሮ የሚያስብቡበትን መንገድ ማስለወጥ ነው።

አንዲት ለግላጋ ሴት ጠረጴዛው ላይ ስትንጋለል አንደኛው ዘራፊ "እባክሽ እንደ ሰለጠነ ሰው ሁኚ። ለዘረፋ እንጂ ሴት ለመድፈር አልመጣንም!" ብሎ ጮኸባት።

ይህ ደግሞ "Being Professional" ተብሎ ይጠራል። የሰለጠንክበትን አጀንዳ ብቻ ማስፈፀም። ከዛ ውጭ ልታተኩርበት የሚገባ ነገር ካለ ዓላማህን መሳት ነው።

የዘራፊዎቹ ቡድን ወደ ቤታቸው ከተመለሱ ቡኃላ በዕድሜ አነስ የሚለው ማስትሬት ዲግሪ ያለው ብልህ ብላቴና በዕድሜ ትልቁን ዘራፊ (6ኛ ክፍል ብቻ ያጠናቀቀውን ጎልማሳ) "ታላቅ ወንድሜ ያገኘነውን ገንዘብ እንቁጠረው።" አለው።

ትልቁ ሌባ "ሞኝ ነህ እንዴ? የዘረፍነው ገንዘብ እኮ እጅግ ብዙ ነው ይሄን ሁሉ ስንቆጥር ቀናትም አይበቃንም። ማታ በTV የዘሩፍነው ገንዘብ መጠን በዜና ይገለፅ የለ እንዴ?" አለው

ይህ "Experience" የምንለው ነው። ዛሬ ዛሬ ከወረቀት ማስረጃ ይልቅ ልምድ ቦታ የሚሰጥበት አጋጣሚዎች አሉ።

ዘራፊዎቹ ከባንኩ እንደወጡ የባንከ ማናጀር ለሱፐርቫይዘሩ "በል በቶሎ ለፖሊስ ደውልና ዘረፋውን በአስቸኳይ አሳውቅ።" አለው። ሱፐርቫይዘሩ ግን "ቆይ ከካዝናው ውስጥ 10 ሚሊዮን ብር ለራሳችን እናውጣና ሌቦቹ ከወሰዱት 70 ሚሊዮን ብር ላይ ጨምረን ሪፖርት ብናደርግ ይሻላል።" አለ።

ይህ ደግሞ "Swim with the tide" ይባላል። የማይመቹ አጋጣሚዎችን ለራስህ አድቫንቴጅ በመውሰድ ራስህን መጥቀም ነው።

ሱፐርቫይዘሩ በአጋጣሚው ያገኙትን ሀብት ሲመለከት "ኧረ እንደውም በየወሩ ባንክ ቢዘረፍ አሪፍ ነው።" አለ

ይህ ደግሞ "Killing Bordem" ይባላል። ባልተጠበቁ አጋጣሚዎች ከአቅምህ በላይ የሆኑ ነገሮች ሲከሰቱ ከሙያህና ከስራህ ይልቅ ለግል ደስታህ ቅድሚያ መስጠት ነው።

በቀጣዩ ቀን በሀገሪቱ ብሔራዊ የTV ጣብያ ዜና ላይ ከባንኩ 100 ሚሊዮን መዘረፉ ተነገረ። ዘራፊዎቹ በተደጋጋሚ ቢቆጥሩ ቢቆጥሩ 20 ሚሊዮን ብር ብቻ ሆነ የዘረፉት። በጣም ተናደዱ እጅግ ተበሳጩ። "እኛ ሕይወታችንን ነፍሳችንን አደጋ ላይ ጥለን የዘረፍነው 20 ሚሊዮን ብር ብቻ ነው። የባንክ ማናጀሩ ግን 80 ሚሊዮን ብር በኛ ስም በነፃነት በእጆቹ ወሰደ። ሌባ ከመሆንማ መማር የተማረ መሆን ይሻላል" አሉ።

ይህ ደግሞ "Knowledge is worth as much as Gold" እውቀት እንደ ወርቅ ውድ መሆኑን የምታውቅበት ነጥብ ነው።

በመጨረሻ የባንክ ማናጀሩ እና ሱፐርቫይዘሩ ደስተኞች እና ሳቂታዎች ነበሩ።

አሚር ሲራጅ ከAfrican Nomad ገፅ እንደተረጎመው

ከላይ ካሉት ከ6 ነጥቦች የትኛው ይበልጥ አስፈላጊ ነው?

02/07/2022

Address

Addis Ababa
1000

Telephone

+251964651484

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Visit Gurage posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Visit Gurage:

Share