29/03/2026
ኢትዮጵያ ለአለም ንግድ ድርጅት አባልነት የመጨረሻው መስመር ላይ መድረሷ ተገለፀ
ኢትዮጵያ ለዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት የመጨረሻው መስመር ላይ መድረሷ ተገለጸ
: ለዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ድርድር ላይ የቆየችው ኢትዮጵያ የመጨረሻው መስመር ላይ መድረሷ ተገለጸ፡፡
በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትሩ ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) የሚመራው የኢትዮጵያ ልዑክ ለካሜሩን ያውንዴ እየተካሄደ ባለው 14ኛው የዓለም ንግድ ድርጅት የሚኒስትሮች ኮንፍረንስ እየተሳተፈ ነው፡፡
የልዑክ ቡድኑ አባል ከሆኑት መካከል የብሔራዊ ባንክ ገዥ ኢዮብ ተካልኝ የዓለም የንግድ ድርጅትን ጠቅሰው በጻፉት ጽሑፍ፣ ኢትዮጵያ የዓለም የንግድ ድርጅት አባልነትን ለመቀላቀል የመጨረሻ መስመር ላይ ነች ብለዋል፡፡
መጋቢት 17 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ ለአራት ተከታታይ ቀናት በሚቆየው ኮንፈረንስ፣ የኢትዮጵያ ተደራዳሪ ቡድን ከድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጋር ተገናኝቶ መምክሩን ከቦታው የወጣው መረጃ ያመላክታል፡፡
ከ22 አገሮች ጋር የድርጅቱ አባል ለመሆን ድርድር እያካሄዱ ከሚገኙት አገሮች መካከል ኢትዮጵያ አባልነቱን ለመቀላቀል ጥረት ከጀመረች ሁለት አሥር ዓመታት አልፈዋታል፡፡
የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ኒጎዚ አኮንጁ አባልነቱን ለመቀላቀል ጥረት ከሚያደርጉት አገሮች መካከል ኢትዮጵያና ኡዝቤኪስታን ከፍተኛ የሆነ ተግባር የሠሩ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
ኢትዮጵያ መሠረታዊ የሚል የድርድር ሒደትን በማከናወን ለአባልነቱ መቃረቧን የገለጹ ሲሆን፣ ያልተገደበ የፖለቲካ ቁርጠኝነት መኖሩ ተገልጿል፡፡ ኢትዮጵያ የደረሰችበት ወሳኝ ምዕራፍ የኢትዮጵያን ወደ አባልነት የመቀላቀል ሒደት ግልጽ ተስፋና እምነት መኖሩን የሚያመለክት ነው ተብሏል፡፡
ኢትዮጵያ አጠቃላይ ለአባልነቱ መሳካት ባለፈው አንድ ዓመት ብቻ ያደረገችው ጥረት ...
🔗 ተጨማሪ ያንብቡ: https://ethiopianreporter.com/153976/
----------||----------
የሪፖርተር ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ
ፌስቡክ ↠ bit.ly/2Iv9bZB
ትዊተር ↠ bit.ly/35qeNwV
ሊንክድኢን ↠ bit.ly/3S0k6uB
ኢንስታግራም ↠ bit.ly/44Iiuxb
ቴሌግራም ↠ bit.ly/3Qb4N1M
ዩቲዩብ ↠ bit.ly/3p0jUQY
ቲክቶክ ↠ bit.ly/3Ruxsyv
ትሬድስ ↠ bit.ly/466VBCG
🧾 የስራ ማስታወቂያዎች ↠ EthiopianReporterJobs.com
📢 የጨረታ ማስታወቂያዎች ↠ ReporterTenders.com
📩 ለዜና ጥቆማ እና መረጃ፡ [email protected]
✍️ ነጻ ፕሬስ፣ ነጻ ሐሳብ፣ ነጻ መንፈስ