Public Service Transport Service / ፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት

  • Home
  • Ethiopia
  • Addis Ababa
  • Public Service Transport Service / ፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት

Public Service Transport Service / ፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት ኢትዮጵያ ፣ አዲስ አበባ ፣ ሜክሲኮ ከ ፖሊስ ሆስፒታል ፊትለፊት

አገልግሎቱ የ2018 ዓ.ም እቅድ አፈፃፀምን ገምግሞ የ2019 እቅድን አስተዋወቀ// የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት ሀምሌ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ከህዝብ ክንፍ አባላት፣ ከመንግስት ...
06/08/2026

አገልግሎቱ የ2018 ዓ.ም እቅድ አፈፃፀምን ገምግሞ የ2019 እቅድን አስተዋወቀ//

የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት ሀምሌ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ከህዝብ ክንፍ አባላት፣ ከመንግስት ተቋማትና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር የ2018 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም እና የ2019 በጀት ዓመት እቅድ በተመለከተ ሰፊ የግምገማና የውይይት መድረክ እንዲሁም የእውቅና ፕሮግራም አከናወነ።


የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ አስካለ ተክሌ ከህዝብ ክንፍና ከባለድርሻ አካላት ጋር ትውውቅ ካደረጉ በኋላ ፕሮግራሙን በንግግር ከፍተዋል፡፡

ዋና ዳይሬክተሯ በመክፈቻ ንግግራቸው የ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀምን መገምገም ያለፈውን ለመተንተን ብቻ ሳይሆን ከተገኙ ጥንካሬዎችና ድክመቶች በመማር የ2019 በጀት ዓመት ስራዎችን በተሻለ መልኩ ለማሳካት የሚያግዝ መሆኑን ገልጸው የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የከተማዋን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ የሚደግፍ መሰረታዊ አገልግሎት በመሆኑ ጥራቱን፣ ተደራሽነቱንና ቀልጣፋነቱን ማሳደግ የሁሉም ባለድርሻ አካላት የጋራ ኃላፊነት መሆኑን አስገንዝበዋል።


በተጨማሪም በ2019 በጀት ዓመት የተቀመጡ እቅዶችን ለማሳካት የህዝብ ክንፍ፣ የመንግስት ተቋማት፣ የጸጥታና የትራፊክ ቁጥጥር አካላት እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት ያላቸው ተሳትፎ ትብብር ወሳኝ መሆኑን ጠቁመዋል።


የአገልግሎቱ የእቅድና ገበያ ጥናት ዳይሬክቶሬት ቡድን መሪ የሆኑት አቶ መክዩ አክመል ባቀረቡት ሪፖርት በ2018 በጀት ዓመት የተከናወኑ ዋና ዋና ስራዎች፣ የተመዘገቡ ውጤቶች፣ ያጋጠሙ ተግዳሮቶችና ከእነዚህ የተገኙ ተሞክሮዎች በዝርዝር ቀርበዋል::

በተጨማሪም በ2019 በጀት ዓመት የአገልግሎት ጥራትን ማሻሻል፣ የህዝብ እርካታን ማሳደግ፣ ተቋማዊ አቅምን ማጠናከር እና ከባለድርሻ አካላት ጋር ያለውን ትብብር ይበልጥ ማጎልበት በዋናነት ትኩረት እንደሚሰጣቸውም ተገልጸዋል።


የዲጂታል መታወቂያ አጠቃቀምን በተመለከተ በአገልግሎቱ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በወ/ሮ ሰሚራ ሁሴን ማብራሪያ ተሰጥቶበታል፡፡

ውይይቱን የመሩት የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ አስካለ ተክሌ እና የትራንስፖርት አገልግሎት ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ወ/ሪት ቤዛዊት ተሾመ እንዲሁም የሀብት ምደባና አጠቃቀም ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ዘውዱ አሰፋ ሲሆኑ በቀረበው ሪፖርትና እቅድ ዙሪያ ከተሳታፊዎች ለተነሱጥያቄዎች ሀሳቦችና አስተያየቶችምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ተሳታፊዎችም በቀረበው ሪፖርትና በቀጣዩ ዓመት እቅድ ላይ ገንቢ አስተያየቶችን በማቅረብ በተቀናጀ አሰራር የተሻለ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት በጋራ እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል።

በመድረኩ መጨረሻ በ2018 በጀት ዓመት የላቀ አፈፃፀም ላሳዩ ለ11 ክፍለ ከተሞች የትራፊክ ቁጥጥር መምሪያ እና ለመንግስት ተቋማት እንዲሁም ለኮማንድ ፖስት አባላት የእውቅና የምስክር ወረቀት ተሰጥቷል፡፡

04/08/2026

💚🇪🇹

03/08/2026

ኢትዮጵያ በአንድ ጀምበር 805.3 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል አዲስ ደማቅ ክብረ ወሰን አስመዘገበች።

03/08/2026

የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር እና ሚኒስትር ዴኤታዎች በዛሬው የ2018 ዓ.ም አረንጓዴ አሻራ ተስፉን ሲተክሉ … 🌳🌱🇪🇹
Ministry of Transport and Logistics - Ethiopia
Public Service Transport Service / ፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት Bareo Hassen
#አረንጓዴአሻራ #ተስፋንእንትከል

03/08/2026

ተስፉን እንትከል! የ2018 ዓ.ም አረንጓዴ አሻራ! 🌳🌱
Public Service Transport Service / ፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት
#አረንጓዴአሻራ

03/08/2026
የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር የትራንስፖርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ Bareo Hassen በዛሬው የአረንጓዴ አሻራ መርሀ - ግብር ተሳትፎ ላይ ያስተላለፉት መልዕክት … 👇“...
03/08/2026

የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር የትራንስፖርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ Bareo Hassen በዛሬው የአረንጓዴ አሻራ መርሀ - ግብር ተሳትፎ ላይ ያስተላለፉት መልዕክት … 👇

“ዝናብ ሳይበግረን ለሊት ተነስተን ለሀገራችን አዲስ ተስፋ ተክለናል! 🌱

በዛሬው ዕለት በተካሄደው የ800 ሚሊዮን ችግኝ የአንድ ቀን ታሪካዊ መርሃ-ግብር ቃላችንን ጠብቀን የሀገራችንን ምድር በአረንጓዴ በማልበስ እና የነገ ተስፋችንን በማፅናት ድንቅ የታሪክ አካል በመሆናችን እንኳን ደስ አለን!

የሚኒስቴር መስሪያ ቤታችን ዋነኛ ዓላማ የሆነውን "የአረንጓዴ ትራንስፖርት" ትግበራ በተግባር እየመራን እንደሆነው ሁሉ ዛሬም ለትውልድ የሚሻገር ትልቅ አገራዊ አሻራን ከሚኒስቴሩ ተጠሪ ተቋማት ጋር በጋራ ሆነን ማኖራችን ትልቅ ኩራትና እርካታ ነው::

ሀገራችንን ይበልጥ አረንጓዴ አድርገናት ለነገው ትውልድ ለምለምና የተዋበች ሀገር ለማስረከብ የምናደርገው ጉዞ በጠንካራ ክንዳችን ይቀጥላል!

አረንጓዴ አሻራ ለተሻለ ነገ! 🇪🇹”

አቶ በርኦ ሀሰን የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ።

ተስፉን እንትከል የ2018 ዓ.ም አረንጓዴ አሻራ! 🌳🌱ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ከተጠሪ ተቋማቱ ጋር በጋራ በመሆን የዛሬውን የአረንጓዴ አሻራ መርሀ-ግብር በንቃትና በላቀ ተሳትፎ ...
03/08/2026

ተስፉን እንትከል የ2018 ዓ.ም አረንጓዴ አሻራ! 🌳🌱

ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ከተጠሪ ተቋማቱ ጋር በጋራ በመሆን የዛሬውን የአረንጓዴ አሻራ መርሀ-ግብር በንቃትና በላቀ ተሳትፎ አከናውነዋል።

#አረንጓዴአሻራ

💚 ለፅናትና ለቀጣይ ትውልድ እናለማለን! 🇪🇹ተስፉን እንትከል - የ2018 ዓ.ም አረንጓዴ አሻራ! 🌳🌱 #አረንጓዴአሻራ
03/08/2026

💚 ለፅናትና ለቀጣይ ትውልድ እናለማለን! 🇪🇹

ተስፉን እንትከል - የ2018 ዓ.ም አረንጓዴ አሻራ! 🌳🌱

#አረንጓዴአሻራ

የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት ሠራተኞች በ800 ሚሊዮን የአንድ ጀንበር ሀገራዊ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በቢሾፍቱ ከተማ አካሄዱ//የአገልግሎቱ ሠራተኞች በ2018 ዓ.ም "ተስፋን ...
03/08/2026

የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት ሠራተኞች በ800 ሚሊዮን የአንድ ጀንበር ሀገራዊ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በቢሾፍቱ ከተማ አካሄዱ//

የአገልግሎቱ ሠራተኞች በ2018 ዓ.ም "ተስፋን እንትከል" በሚል መሪ ቃል በሚካሄደው 800 ሚሊዮን የአንድ ጀንበር ሀገራዊ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሂዷል ።

የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት ሠራተኞች በዛሬው መርሃ ግብር ቡና ፣ፍራፍሬ እና የተለያዩ አትክልቶችን በመትከል ለአካባቢ ጥበቃ፣ ለአረንጓዴ ልማት እና ለአየር ንብረት ለውጥ መከላከል ያለውን ቁርጠኝነት ችግኞችን በመትከል በተግባር አሳይተዋል።

የአገልግሎቱ ሠራተኞችም የተተከሉት ችግኞች እስከሚያድጉ ድረስ ተገቢውን እንክብካቤ ማድረግ የሁሉም ተሳታፊ ኃላፊነት መሆኑን በመግለጽ፣ ችግኞችን መትከል ብቻ ሳይሆን መንከባከብ እንደሚያስፈልግም አሳስበዋል፡፡

Address

Ethiopia, In Front Of Police Hospital
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Public Service Transport Service / ፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share